Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ 3 ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ዛሬ በድሬዳዋ ስታዲዬም ሦስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚሁ መሠረት 3 ሠዓት ከ30 ላይ ሐዋሳ ከተማ ከስሁል ሽረ እንዲሁም 10 ሠዓት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ይጫወታሉ፡፡ ምሽት 1 ሠዓት ላይ ደግሞ ባሕር ዳር ከተማ እና አዳማ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
Read More...

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ፋሲል ከነማ እና መቐለ 70 እንደርታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዩ። በድሬዳዋ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታ ያሬድ ብርሃኑ ባስቆጠራት ግብ ሲመራ ቢቆይም፤ ፋሲል ከነማ ቢኒያም ላንቃሞ ከእረፍት መልስ ባስቆጠራት ግብ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።…

ዋሊያዎቹ የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ኮትዲቯር ላይ ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ጋር የሚያደርጋቸውን የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ 3ኛ እና 4ኛ የምድብ ጨዋታዎች ኮትዲቯር ላይ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡ በዚሁ መሠረት ዋሊያዎቹ 3ኛውን ጨዋታ ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት 1 ሠዓት ላይ ጊኒ የሜዳ ጨዋታዋን ለማድረግ ባስመዘገበችው በኮትዲቯር ያሞሱክሩ በሚገኘው…

ኢትዮጵያ መድንና አርባምንጭ ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሣምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድንና አርባምንጭ ከተማ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያዩ፡፡ በሌላ በኩል ምሽት 1 ሠዓት ላይ ሊደረግ የነበረው የወልቂጤ ከተማ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ÷ የወልቂጤ ከተማ ክለብ ማሟላት የሚጠበቅበትን ባለማሟላቱ ምክንያት ንግድ ባንክ በፎርፌ 3 ነጥብ…

የ2024 የአፍሪካ የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2024 የአፍሪካ የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የፊታችን ጥቅምት ወር ላይ ይካሄዳል፡፡ ከጥቅምት 2 እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በሚካሄደው ሻምፒዮና ላይ ከ300 በላይ ስፖርተኞችና ተጋባዥ እንግዶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል ተብሏል፡፡ በውድድሩ የሚያሸንፉ ስፖርተኞች የ25…

ራፋዬል ቫራን ጫማ ሰቀለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሪያል ማድሪድ እና ማንቼስተር ዩናይትድ የቀድሞ ተከላካይ ሥፍራ ተጫዋች ራፋዬል ቫራን እግር ኳስ ማቆሙን አስታውቋል፡፡ ቫራን ባለፈው ክረምት የዝውውር መስኮት ማቼስተር ዩናይትድን በመልቀቅ የጣሊያኑን ኮሞ እግር ኳስ ክለብ መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡ በአዲሱ ክለቡ በነበረበት ጊዜ ያጋጠመው ጉዳት ተከትሎም በ31 ዓመቱ ጫማ…

ማንቼስተር ዩናይትድ የኦልድትራፎርድ ስታዲየምን ሊያድስ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ አንጋፋውን የኦልድትራፎርድ ስታዲም በሁለት ቢሊየን ፓውንድ ወጪ ሊያድስ መሆኑን አስታወቀ፡፡ እድሳቱ ሲጠናቀቅ የስታዲየሙ ተመልካች የመያዝ አቅም ከ100 ሺህ በላይ እንደሚሆን ተገልጿል። እንዲሁም ዕድሳቱ ሲጠናቀቅ በዓመት ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።…