Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ደቡብ አፍሪካዊው እግር ኳስ ተጫዋች የመኪና ስርቆት በሚፈጽሙ ወንጀለኞች መገደሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካ እና የካይዘር ችፍስ ተከላካይ መስመር እግር ኳስ ተጫዋች የሆነው ሉክ ፍሉርስ በጆሃንስበርግ ከተማ የመኪና ስርቆት በሚፈጽሙ ወንጀለኞች በጥይት ተመትቶ ህይወቱ ማለፉ ተገለጸ። ክለቡ እንዳስታወቀው÷ የ24 ዓመቱ ተከላካይ በጆሃንስበርግ ከተማ ሆንዲው በተባለው ሰፈር መኪኒናውን ነዳጅ ለመሙላት እየተጠባበቀ በነበረበት ወቅት በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ አልፏል። የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ቃል አቀባይ ማቬላ ማሶንዶ÷ ጥቃቱን መኪናውን ለመውሰድ በሚፈልጉ ወንበዴዎች መፈፀሙን ገልጸዋል።…
Read More...

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በክለቦች ብቻ የሰራው ሀትሪክ 55 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአልናስሩ የፊት መስመር ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በክለቦች ውስጥ ባለው የእግርኳስ ሕይወት በአንድ ጨዋታ ላይ ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር (ሃትሪክ) ያለውን ታሪክ 55 አድርሷል። ትናንት ምሽት በሳኡዲ ፕሮ ሊግ አል ናስር አብሃን 8 ለ 0 በሆነ ውጤት ባሸነፈበት ጨዋታ ሮናልዶ ከእረፍት በፊት ሶስት ጎሎችን በማስቆጠር ሃትሪክ…

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት የተበረከተላትን የኒሻን ሽልማት ተረከበች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት የተበረከተላትን የወርቅ ጨረር ያለው የኒሻን ሽልማት ተረክባለች። ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በስፖርት ዲፕሎማሲ ላበረከተችው አስተዋፅኦ ቀደም ሲል ከጃፓን መንግስት የክብር ኒሻን ሽልማት የተበረከተላት መሆኑ ይታወሳል፡፡ በጃፓን እና…

ለ45ኛው የዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ልዑክ የእውቅና መርሐግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰርቢያ ቤልግሬድ በተካሄደው 45ኛ የዓለም አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተሳትፎ በድል ለተመለሰው የልዑካን ቡድን የእውቅናና የማበረታቻ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡ በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ÷የተገኘው ውጤት አበረታች መሆኑን በመግለፅ ለቀጣይ ውድድሮች ትኩረት…

በ45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፉ አትሌቶች አቀባበል ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰርቢያ ቤልግሬድ በተካሄደው 45ኛው የዓለም ሀገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተሳተፉ አትሌቶች በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል፡፡ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ለአትሌቲክስ ቡድኑ…

ኢትዮጵያ የቦክስ ስፖርት ውጤታማ እንዲሆን ከፕሮጀክት ጀምሮ ሊሰራበት ይገባል – የቦክስ ስፖርተኞች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የቦክስ ስፖርት ውጤታማ እንዲሆን ከፕሮጀክት ጀምሮ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታ በቦክስ ስፖርት ወርቅ ያስገኙት ስፖርተኞች ተናገሩ፡፡ የቦክስ ባለወርቆቹ ቤተልሄም ገዛኸኝ እና ቤተል ወልዴ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷ ከዓመታት ቆይታ በኋላ በሴቶች የቦክስ…

አርሴናል እና ማንቸስተር ሲቲ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ30ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አርሴናል እና ማንቸስተር ሲቲ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ተጠናቋል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም አርሴናል በ65 ነጥብ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሲቲ ደግሞ በ64 ነጥብ 3ኛ ደረጃን ይዟል፡፡ ቀደም ሲል ብራይተንን 2 ለ 1 ያሸነፈው ሊቨርፑል በ67…