Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በማንዴላ ዋንጫ የአፍሪካ ቦክስ ውድድር ኢትዮጵያ 6 ሜዳሊያ በመሰብሰብ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማንዴላ አፍሪካ ቦክስ ውድድር ኢትዮጵያ ሶስት ብርና ሶስት የነሐስ በአጠቃላይ ስድስት ሜዳልያ በማግኘት ውድድሩን አጠናቃለች። በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያ በሱራፌል አላዩ፣ ሚሊዮን ጨፎ እና ቤተል ወልዱ የነሃስ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡ ቤተልሄም ገዛህኝ፣ ሮማን አሰፋ እና ተመስገን ምትኩ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ቦክስ ለልዑካን ቡድን ሚያዝያ 15 ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ በቦሌ ዓለማቀፍ አውሮፕላን…
Read More...

ማንቼስተር ዩናይትድ እና ማንቼስተር ሲቲ ለዋንጫ ይፋለማሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ እና ማንቼስተር ሲቲ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን ለማንሳት ይፋለማሉ፡፡ ማንቼስተር ዩናይትድና ኮቬንትሪ ሲቲ ዛሬ ያደረጉት ጨዋታ መደበኛና በጭማሪ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 3 አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መለያ ምት አምርተዋል፡፡ በዚህም ዩናይትድ በመለያ ምት 4 ለ 2 በማሸነፍ ለዋንጫው መፋለም የሚያስችለውን ድል…

ሊቨርፑል ፉልሃምን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፉልሃምን የገጠመው ሊቨርፑል 3ለ 1 አሸንፏል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው አጋማሽ አንድ አቻ ሆነው ወደ መልበሻ ክፍል ቢያመሩም ከዕረፍት መልስ ሊቨርፑል ባስቆጠራቸው 2 ጎሎች ፉልሃም ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ ሊቨርፑል ማሸነፉን ተከትሎም በ74 ነጥብ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር እኩል…

ኤቨርተን፣ ክሪስታል ፓላስ እና አስቶንቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሄዱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ኤቨርተን፣ ክሪስታል ፓላስ እና አስቶንቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ በዚህም ኤቨርተን ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ÷ ክሪስታል ፓላስ ዌስትሃምን 5 ለ 2 ረትቷል፡፡ እንዲሁም ከመመራት ተነስቶ አስቶንቪላ ቦርንማውዝን 3 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና እና መቻል አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የተገናኙት ኢትዮጵያ ቡና እና መቻል አንድ አቻ ተለያይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናን ጎል አማኑኤል አድማሱ በጨዋታ ሲያስቆጥር የመቻልን ጎል ደግሞ ምንይሉ ወንድሙ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል፡፡

በ41 ዓመቱ ፈጣኑን የማራቶን ሠዓት ያስመዘገበው አትሌት – ቀነኒሳ በቀለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በለንደን በተካሄደው የማራቶን ውድድር ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ከ2019 ወዲህ ፈጣኑን ሠዓት በማስመዝገቡ አድናቆት ተችሮታል፡፡ አትሌት ቀነኒሳ የዛሬውን የለንደን ማራቶን ውድድር 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል፡፡ የዓለም አትሌቲክስም አትሌቱ…

አትሌት ጫላ ረጋሳ የቪዬና 2024 ማራቶንን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጫላ ረጋሳ የቪዬና 2024 የማራቶን ውድድርን 2 ሠዓት ከ6 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ በመግባት በበላይነት አጠናቀቀ፡፡ በተመሳሳይ በለንደን በተካሄደ የወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቋል፡፡ እንዲሁም አትሌት ትዕግስት አሰፋ…