ስፓርት
ሊቨርፑልና ቼልሲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳቸው የተጫወቱት ሊቨርፑልና ቼልሲ ድል ቀናቸው።
ብራይተንን ያስተናገደው ቼልሲ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
በተመሳሳይ በሜዳው የተጫወተው ሊቨርፑል ፉልሃምን አስተናግዶ 4 ለ 3 አሸንፏል።
በርንማውዝ አስቶቪላን አስተናግዶ 2 ለ2 ሲለያይ፤ ክሪስታል ፓላስን ያስተናገደው ዌስት ሃም 1 ለ 1 ተለያይቷል።
Read More...
በቫሌንሺያ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቫሌንሺያ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በወንዶቹ አትሌት ሲሳይ ለማ ርቀቱን 2 ሰአት ከ1 ደቂቃ ከ48 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ውድድሩን አጠናቋል፡፡
ኬንያዊው አትሌት አሌክሳንደር ሙቲሶ ሁለተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያዊው አትሌት ዳዊት ወልዴ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡…
አርሰናል ዎልቭስን በማሸነፍ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት አጠናከረ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ14ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ዎልቭስን 2 ለ 1 በማሸነፍ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት አጠናክሯል፡፡
ምሽት 12፡00 ላይ በተደረገው ጨዋታ ቡካዮ ሳካ እና ማርቲን ኦዲጋርድ የአርሰናልን ጎሎች ሲያስቆትሩ ማቲያስ ኩና የዎልቭስን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡
ውጤቱን ተክትሎም በውድድሩ ጥሩ ጊዜን እያሳለፈ…
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባሕርዳር ከተማ ድል ቀናው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ ባሕዳር ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
9፡00 ላይ በተደረገው ጨዋታ ለባሕዳር ከተማ ፍራኦል መንግሥቱ እና ቸርነት ጉግሳ እንዲሁም ለቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ አማኑኤል ተርፉ ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡
በጨዋታው ላይ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ ሞሰስ አዶ ባሳየው ያልተገባ ባህሪ…
በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ ሲያሸንፍ ወላይታ ድቻና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ውድድሮች ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የኢትየጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ተጀምሯል፡፡
ወላይታ ድቻ እና ድሬዳዋ ከተማ 9 ሰዓት ላይ ባደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ለወላይታ ድቻ ቢንያም ፍቅሩ በ24ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር÷ ድሬዳዋ ከተማን አቻ ያደረገችዋን ግብ…
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከማስታወቂያ ጋር በተያያዘ በአሜሪካ ክስ ተመሰረተበት
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ፍትሕ ዲፓርትመንት በዓለማችን ትልቁ የገንዘብ ምንዛሬ ተቋም የሆነውን ቢናንስ ኩባንያ አስተዋውቋል በሚል በክርስቲያኖ ሮናልዶ ላይ ክስ መስርቷል፡፡
የቢናንስ ኩባንያ ምስረታውን በቻይና ያደረገ ሲሆን÷ የቻይና መንግስት የዲጂታል የገንዘብ ምንዛሬን መከልከሉን ተከትሎ ዋና መስሪያ ቤቱን ወደ ጃፓን በማዞር በዲጂታል…
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በቫሌንሺያ ማራቶን እንደሚሳተፍ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በፈረንጆቹ ታሕሳስ 3 ቀን በሚካሄደው የቫሌንሺያ ማራቶን እንደሚሳተፍ አስታወቀ፡፡
አትሌቱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው ጽሑፍ÷ ከብዙ ጊዜ ጉዳት በኋላ በቫሌንሺያ ማራቶን እንደሚሳተፍ አስታውቋል።
ወደ ሩጫ ለመመለስ ከባድ የልምምድ ጊዜዎችን ማሳለፉን የገለፀው አንጋፋው አትሌት÷ “በፈረንጆቹ…