Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በኒውካስል ግማሽ ማራቶን አትሌት ታምራት ቶላ አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ኒውካስል በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ታምራት ቶላ አሸንፏል፡፡ አትሌት ታምራት ቶላ ርቀቱን 59 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነው፡፡ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሙክታር እድሪስ ደግሞ ርቀቱን 1 ሰዓት 01 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ 3ኛ ደረጃን ይዟል፡፡ በውድድሩ የቤልጂዬሙ አትሌት በሽር አብዲ 2ኛ ሲወጣ÷ ለእንግሊዝ የሚሮጠው ትውልደ ሶማሊያዊው አትሌት ሞ ፋራህ ደግሞ 4ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁን ቢቢሲ…
Read More...

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በግብፅ አቻው ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት በተካሄደው በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በግብፅ አቻው 1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2023 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታ ከግብጽ አቻው ጋር አካሂዷል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታቸውን በካይሮ አየር ሃይል ስታዲየም ምሽት 1 ሰዓት ላይ አድርገዋል፡፡ ውጤቱን…

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከግብፅ አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከግብፅ አቻው ጋር ዘሬ ምሽት ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ አስቀድሞ ከአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ውጪ መሆኑን ያረጋገጠው ብሔራዊ ቡድኑ÷ መርሐ ግብሩን ለማከናነወን ከቀናት በፊት ካይሮ መግባቱ ይታወሳል፡፡ የዋሊያዎቹ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ዳንኤል ገብረማሪያም ከጨዋታው አስቀድመው በሰጡት…

የ2023ቱ የባሎንዶር ኮከብ ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2023ቱ የባሎንዶር ኮከብ ተጫዋቾች ዝርዝር ትላንት ምሽት ይፋ ተደርጓል፡፡ 30 ተጫዋቾች በቀረቡበት የባሎዶር የኮከቦች ዕጩ ዝርዝር ውስጥ የአምስት ጊዜ አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከፈረንጆቹ 2003 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ አለመካተቱ ተገልጿል፡፡ በአንጻሩ የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ እና በማንቼስተር ሲቲ ድንቅ…

አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ በ2024 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከቡሩንዲ ጋር መስከረም 9 እና 15 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚያደርጋቸው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ዝግጅት ለማድረግ ነው ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ የቀረበው፡፡ በዚሁ መሠረት በግብ…

የማንቼስተር ዩናይትድ ዋጋ በ500 ሚሊየን ፓውንድ ዝቅ ማለቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የላንክሻየሩ ክለብ ማንቼስተር ዩናይትድ የሽያጭ ዋጋው በ500 ሚሊየን ፓውንድ ዝቅ ማለቱ ተገልጿል፡፡ የክለቡ ዋጋ በአሜሪካው የኒዎርክ የአክሲዮን ሽያጭ በ500 ሚሊየን ፓውንድ ወይም በ628 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ዝቅ ማለቱ ተጠቅሷል፡፡ ክለቡ በአርሰናል ከተሸነፈ በኋላ መልበሻ ክፍል ውስጥ አለመግባባቶች ተፈጥረው…

ዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ካይሮ ገብተዋል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አባላት ከግብፅ አቻቸው ጋር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ መርሐ ግብርን ለማከናወን ካይሮ ገብተዋል፡፡ የብሄራዊ ቡድኑን ተጫዋቾች እና አመራሮችን የያዘው ልዑክ ከ3 ሰዓታት በላይ በረራ በኋላ ካይሮ በሰላም መግባቱን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ቀደም ሲል ባደረጉት ጨዋታ ዋሊያዎቹ በዳዋ…