ስፓርት
ሉሲዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታውን ቀን 9 ሰዓት ከብሩንዲ አቻው ጋር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ያካሂዳል ።
በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚሰለጥነው ብሔራዊ ቡድኑ÷ 26 ተጫዋቾችን በመያዝ ዝግጅቱን ከጳጉሜን 3 ቀን ጀምሮ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሲያደርግ ቆይቷል።
ከሀገር ውስጥ ቡድኖች ጋርም የተለያዩ የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችሲያደርግ የቆየው ብሄራዊ ቡድኑ÷ ለዛሬው ጨዋታ የመጨረሻ ልምምዱን ትናንት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ማከናወኑ የሚታወስ…
Read More...
በሪጋ 2023 የጎዳና ላይ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይጠበቃሉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በላቲቪያ ሪጋ በሚካሄዱ የጎዳና ላይ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የማሸነፍ ቅድመ ግምት ተሰጥቷቸዋል፡፡
በጎዳና ውድድሩ አምስት የዓለም ሪከርድ የሰበሩ አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን÷ የኦሎምፒክ እና የዓለም ሻምፒዮን አትሌቶችን ጨምሮ 347 አትሌቶች በስድስት ርቀቶች ይሳተፋሉ፡፡
ከመስከረም 20 እስከ 21 ቀን 2016…
ለዓመታት ከአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ርቆ የቆየው አርሴናል 4 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለስድስት ዓመታት ከአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ርቆ የቆየው አርሴናል በምድብ ማጣሪያ ጨዋታው ፒ ኤስ ቪ አይንዶቨንን 4 ለ 0 አሸንፏል።
በተመሳሳይ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ2023/24 የውድድር አመት የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው ባየር ሙኒክ ተጋጣሚውን ማንቼስተር ዩናይትድን 4 ለ 3 በሆነ ውጤት ረትቷል።…
ሪያል ማድሪድ ዩኒየን በርሊንን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምሽቱን በተካሄደው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ተጋጣሚውን ዩኒየን በርሊንን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ጁዲ በሊንግ ሃም በተጨማሪ ሰዓት የማድሪድን ብቸኛ ጎል ከመረብ አሳርፏል፡፡
በሌላ በኩል ኮፕንሀገን ከጋላታሳራይ ጋር ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
#Ethiopia…
አርሰናል ከ6 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታውን ዛሬ ምሽት ያደርጋል
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 9 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ ከ6 ዓመታት ቆይታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታውን ከኔዘርላንድሱ ፒኤስ ቪ ኢንድሆቭን ጋር ዛሬ ምሽት ያደርጋል፡፡
አርሰናል ለመጨረሻ ጊዜ በመድረኩ ተሳትፎ ያደረገው በፈረንጆቹ 2017 ሲሆን÷ በዚህም በጀርመኑ ክለብ ባየርሙኒክ ከምድብ ተሸንፎ መሰናበቱ የሚታወስ ነው፡፡
በማይክል…
በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ባህር ዳር ከተማ ድል ቀናው
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 6 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ቅድመ ማጣሪያ ባህር ዳር ከተማ ድል ቀንቶታል።
ባህር ዳር ከተማ ከቱኒዚያው ክለብ አፍሪካን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2 ለ 0 አሸንፏል።
የድል ጎሎቹን ሀብታሙ ታደሰ ከእረፍት በፊት እና በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ አስቆጥሯል።
የመልሱ ጨዋታ ከቀናት በኋላ የሚካሄድ…
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት የ ጄ ኬ ኤስ የካራቴ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት የ ጄ ኬ ኤስ (jks) የካራቴ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡
በዱባይ እየተካሄደ ባለው የእስያ አፍሪካ ዋንጫ የjks የካራቴ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆኑት ሶስት ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች ሜዳሊያ አግኝተዋል።
በመድረኩ በ60 ኪሎ ግራም የተወዳደረው ናትናኤል…