Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ለኢንተርናሽናል ዳኝነት የተመረጡ ኢትዮጵያውያን ዳኞች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢንተርናሽናል ዳኝነት የተመረጡ ኢትዮጵያውያን ዳኞች ዝርዝር ይፋ ሆኗል፡፡ በዓለም አቀፍ መድረክ ኢትዮጵያን የሚወክሉ በወንዶች ሰባት ዋና እና ሰባት ረዳት እንዲሁም በሴቶች አራት ዋና እና አራት ረዳት ዳኞች ተመርጠው ለፊፋ ዳኞች ኮሚቴ መላካቸው ይታወቃል። የዓለም ዓቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበርም ከአንድ ወንድ ረዳት ዳኛ ውጭ ሌሎች እጩ ዳኞች ለኢንተርናሽናል ዳኝነት እንደተመረጡ ማስታወቁን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡ በዚህ መሰረትም፡- በወንድ ዋና ዳኝነት፡-…
Read More...

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከተማን 3 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስምንተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከተማን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ቀን 9 ሰዓት በተደረገው ጨዋታ አቤል ያለው የቅዱስ ጊዮርጊስን ሶስት የድል ጎሎች ከእረፍት በፊት በማስቆጠር ሃትሪክ ሰርቷል፡፡ በዚህም አቤል ያለው በ2016ቱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ከባህርዳር ከተማው አጥቂ ሀብታሙ ታደሰ…

የሜሲ መለያዎች በ10 ሚሊየን ዶላር

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲናዊው የእግርኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በ2022ቱ የኳታር ዓለም ዋንጫ የለበሳቸው መለያዎች ለጨረታ ቀርበዋል፡፡ ከትላንት ጀምሮ በተከፈተው እና ዛሬ ምሽት ይጠናቀቃል በተባለው ጨረታ አርጀንቲናዊው ኮከብ በዓለም ዋንጫው የለበሳቸው መለያዎች 10 ሚሊየን ዶላር ወይም 8 ሚሊየን ዩሮ እንደሚሸጡ ተጠብቋል፡፡ የሜሲ 6…

ቪክተር ኦሲሜን የአፍሪካ ኮኮብ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) ናይጄሪያዊዉ የናፖሊ አጥቂ ቪክተር ኦሲሜን የ2023 የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል። በጣሊያን ሴሪ አ የ2022/23 የውድድር ዘመን ኦሲሜን የስኩዴቶው ሻምፒዮን ከሆነው ናፖሊ ጋር ምርጥ ጊዜን ያሳለፈ ሲሆን፥ 26 ጎሎችን በማስቆጠር የሴሪ ኤው ኮከብ ጎል አግቢ እንደነበር አይዘነጋም። በሌላ በኩል ሞሮኳዊው በረኛ…

አትሌት ትዕግስት አሰፋ የዓለም ምርጥ አትሌት ሽልማትን አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ከስቴዲየም ውጭ ባሉ ውድድሮች ባሳየችው ድንቅ የሆነ ብቃት የዓመቱ ምርጥ አትሌት መባሏን የዓለም አትሌቲክስ ይፋ አድርጓል። አትሌት ትዕግስት በሴቶች ማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለቤት እንደሆነች ይታወቃል። ከቀናት በፊት ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በስፖርታዊ ጨዋነት ማሸነፏ…

ማህበሩ የ7ኛ ሣምንት የዲስፕሊን ውሳኔዎችን ይፋ አድርጓል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ አክሲዮን ማህበር በ7ኛ ሣምንት ጨዋታዎች የተላለፉ የዲስፕሊን ውሳኔዎችን ይፋ አድርጓል፡፡ በሣምንቱ መርሐ ግብር በተደረጉ ሠባት ጨዋታዎች ስድስቱ በመሸናነፍ እንዲሁም አንድ ጨዋታ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቅ 16 ጎሎች በ14 ተጫዋቾች ተቆጥሯል። በተጨማሪም 28 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ…

ዝላታን ኢብራሂሞቪች የኤሲ ሚላን የቦርድ አባል ለመሆን መስማማቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ስዊድናዊው አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች የጣሊያኑን ኤሲ ሚላን በቦርድ አባልነት ለመቀላቀል መስማማቱ ተገልጿል፡፡ እስከ 41 ዓመቱ ድረስ በኢንተርናሽናል እግር ኳስ የዘለቀው ግዙፉ አጥቂ ባለፈው ክረምት ራሱን ከእግር ኳስ ዓለም ማግለሉ የሚታወስ ነው፡፡ ከእግር ኳሱ ከተገለለ በኋላ ከክለቡ ጋር ግንኙነቱን ያላቋረጠው…