ስፓርት
ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና በአቻ ውጤት ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ በአንድ አቻ ውጤት ተለያዩ፡፡
በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደውየ28ኛ ሣምንት መርሐ ግብር÷ 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫውተዋል፡፡
በተጠባቂው ደርቢ ጨዋታም ኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስን ግብ እስማኤል ኦሮ አጎሮ 66ኛው ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥር÷ የኢትዮጵያ ቡናን ደግሞ ብሩክ በየነ በ72ኛው ደቂቃ ላይ…
Read More...
በሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ የማራቶን ውድድር አትሌት ብርሃኑ ነበበው እና ጠጅቱ ስዩም አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ ማራቶን ውድድር አትሌት ብርሃኑ ነበበው እና አትሌት ጠጅቱ ስዩም አሸነፉ።
39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ የማራቶን ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ ሰሚት ለስላሳ ፋብሪካ ተብሎ የሚጠራው ቦታ መነሻና መድረሻው አድርጎ ተካሂዷል፡፡
በማራቶን ውድድሩ በወንዶች አትሌት ብርሃኑ ነበበው…
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከብሔራዊ ቡድኑ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኋላ ዛሬ ይመለሳል፡፡
በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በሚካሄደው የ28ኛ ሣምንት መርሐ ግብር÷ 9፡00 ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ይገናኛሉ፡፡
12፡00 ላይ ደግሞ ባሕርዳር ከነማ ከሲዳማ ቡና እንደሚጫወቱ…
39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን ውድድር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን ውድድር መካሄድ ጀምሯል፡፡
ውድድሩ እየተካሄደ የሚገኘው በአዲስ አበበባ ሲሆን÷ መነሻ እና መድረሻውን ሰሚት ማድረጉም ተገልጿል፡፡
በውድድሩ÷ 12 ክለቦች፣ 2 ክልሎችና 1 ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 354 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ እየተሳተፉ ነው፡፡
ለውድድሩ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ…
39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን ውድድር የፊታችን እሁድ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 39ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን ውድድር ሰኔ 18 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡
መነሻ እና መድረሻውን ሰሚት በሚያደርገው የማራቶን ውድድር ÷ 12 ክለቦች፣ 2 ክልሎችና 1 ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 354 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ ይካፈሉበታል።
ለውድድሩ…
የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር በመቀሌ ከተማ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የሚሳተፉበት የ2015 የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ በመቀሌ ከተማ ተጀምሯል።
ውድድሩን የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ወንድሙ ሃይሌና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የማህበራዊ ልማት ሽግግር ሃላፊ ክንደያ ገብረሕይወት (ፕ/ር) አስጀምረዋል።
አቶ ወንድሙ ሃይሌ…
የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት አትሌቲክስ ሻምፒዮና የፍጻሜ ውድድሮች ተከናወኑ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተጀመረው 3ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት አትሌቲክስ ሻምፒዮና በተለያዩ ርቀቶች የፍጻሜ ውድድሮች ተከናውነዋል፡፡
በዚሁ መሰረት በ10 ሺህ ሜትር የወንዶች ውድድር÷ አቤል በቀለ ከተንታ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 1ኛ፣ ኃይሌ ጥጋቡ ከደብረ ብርሃን አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል 2ኛ እንዲሁም አንዳርጋቸው…