Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለብሄራዊ ቡድን 200 ጊዜ በመሰለፍ የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ሰፈረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን 200 ጊዜ ተሰልፎ በመጫዎት ስሙ በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ሰፍሯል፡፡ ሮናልዶ ትላንት ምሽት በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ሀገሩ ፖርቹጋል አይስላንድን በገጠመችበት ጨዋታ 200ኛ ጨዋታውን ለብሄራዊ ቡድኑ አድርጓል፡፡ በጨዋታውም ግብ አስቆጠሮ ሀገሩን አሸናፊ ማድረግ መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡ ይህን ተከትሎም ሮናልዶ በወንዶች ምድብ ለብሄራዊ ቡድን ብዙ ጊዜ የተሰለፈ ተጫዋች በመሆን  የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ሰርተፍኬትን ከጨዋታው በኋላ…
Read More...

ኢትዮጵያ እና ማላዊ በአቻ ውጤት ተለያ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ እና ማላዊ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዩ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አምስተኛ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ከማላዊ አቻው ጋር አከናውኗል፡፡ የሁለቱ አገራት ጨዋታ በሞዛምፒክ ዚምፔቶ ብሔራዊ ስታዲየም ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ተደርጓል፡፡…

ኢትዮጵያ ከማላዊ ጋር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዋን እያደረገች ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አምስተኛ የምድብ ጨዋታውን ከማላዊ አቻው ጋር እያካሄደ ነው፡፡ ጨዋታው በሞዛምፒክ ዚምፔቶ ብሔራዊ ስታዲየም ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡ በኮትዲቭዋር አስተናጋጅነት በፈረንጆቹ 2024 በሚካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ በምድብ 4 የማጣሪያ ጨዋታዋን እያደረገች ያለችው…

ቼልሲ ንኩንኩን ሲያስፈርም አርሰናል ለራይስ 90 ሚሊየን ፓውንድ አቅርቧል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የአውሮፓ ክለቦች በቀጣዩ ዓመት ተጠናክረው ለመቅረብ በተጫዋቾች ዝውውር በስፋት እየተሳተፉ ነው። በተለይም የዝውውር መስኮቱ የተከፈተላቸው የእንግሊዝ ክለቦች ራሳቸውን እያጠናከሩ ሲሆን÷ በዚህም ቼልሲ ፈረንሳዊውን አጥቂ ክርስቶፈር ንኩንኩን ከአር ቢ ሌፕዚግ አስፈርሟል። ንኩንኩ ክለቡን ለተረከቡት አሰልጣኝ…

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ለመሆን ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በቀጣዩ ዓመት ፋሲል ከነማን ለማሰልጠን ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡ በ2009 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መሳተፍ የጀመረው ፋሲል ከነማ የሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን የቻለ ሲሆን÷ በ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ ክለቡ በዘንድሮው…

ለ34 የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በ2024 የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግር ኳስ የአፍሪካ ዞን የመጀመርያ ዙር ማጣርያ ከቻድ ጋር ለተደለደለው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 34 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ፡፡ ቡድኑ ለጨዋታው ለሚያደርገው ዝግጅት የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለተጫዋቾቹ ጥሪ አድርገዋል። ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾችም ሰኔ 13 ቀን…

የአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 36 ክለቦች በ71 ምድብ እና በአምስት የውደድር ዘርፍ በሁለቱም ፆታ የሚሳተፉበት የአዲስ አበባ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ተጀመረ፡፡ የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌደሬሽን የበላይ ጠባቂ ማስተር ወጋየሁ በኃይሉ በመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶን ለማሳደግ የክለቦች…