ስፓርት
ዴቪድ ሲልቫ ከእግር ኳስ ራሱን አገለለ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ስፔናዊው የመሀል ክፍል ተጫዋች ዴቪድ ሲልቫ በ37 ዓመቱ ከእግር ኳስ ራሱን አግልሏል፡፡
የቀድሞው የማንቸስተር ሲቲ ባለውለታ ዴቪድ ሲልቫ ከከባድ የቁርጭምጭሚት ጉዳት በኋላ ነው ከኢንተርናሽናል እግር ኳስ ራሱን እንዳገለለ ያስታወቀው፡፡
ሲልቫ በፈረንጆቹ 2010 ከስፔኑ ቫሊንሲያ ማንቸስተር ሲቲን የተቀላቀለ ሲሆን÷ ከቡድኑ ጋር አስር ዓመታትን በማሳለፍ አራት የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል፡፡
ሲልቫ በ2020 ማንቸስተር ሲቲን በመልቀቅ ከስፔኑ ሪያል ሶሽዳድ ጋር ሶስት ዓመታትን…
Read More...
በሴካፋ ከ18 ዓመት በታች የሴቶች የእግር ኳስ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በሴካፋ ከ18 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዩጋንዳ አቻው 1 ለ 0 ተሸንፏል።
በምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ማኅበራት ምክር ቤት(ሴካፋ) ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው ከ18 ዓመት በታች ውድድር ዛሬ በታንዛንያ ዳሬ ሰላም ተጀምሯል።
10 ሺህ…
በኮንፌዴሬሽን ካፕ ኢትዮጵያን የሚወክለው ባህር ዳር ከተማ ተጋጣሚውን አውቋል
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ኢትዮጵያን የሚወክለው ባህር ዳር ከተማ ተጋጣሚውን አውቋል።
ክለቡ በመጀመሪያው ዙር የኮንፌዴሬሽን ማማጣሪያ ከታንዛኒያውአዛም ጋር ጨዋታውን የሚያደረግ ይሆናል።
ይህን ጨዋታ ካሸነፈ ደግሞ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ደግሞ ከቱኒዚያው ክለብ አፍሪካ ጋር እንደሚገናኝ ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል።…
ንግድ ባንክ በ2015 ዓ.ም ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች ሽልማት አበረከተ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2015 ዓ.ም በተለያዩ የስፖርት ዘርፎች የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ስፖርተኞች እና ባለሙያዎች የእውቅና እና የማበረታቻ ሽልማት አበርክቷል።
ባንኩ ባለፈው ዓመት በተካሄዱ የአትሌቲክስ፣ እግርኳስና የጠረጴዛ ቴንስ ውድድሮች በድምሩ 38 ዋንጫ ማንሳት የቻለ ሲሆን÷ ለዚህ ውጤት መገኘት አስተዋጽኦ ለነበራቸው…
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀደሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባት በይፋ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ በመሆን ተሹሟል፡፡
ክለቡ ከተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በኋላ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ እና ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር ድርድር መጀመራቸው ሲዘገብ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡
ፋሲል ከነማ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ…
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ በሴቶች የዓለም ዋንጫ አሜሪካን ወክላለች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ ግርማ በሴቶች የዓለም ዋንጫ በአሜሪካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ስብስስብ ውስጥ ድንቅ ብቃቷን እያሳየች ትገኛለች፡፡
የተካላካይ ክፍል ተጫዋቿ በፈረንጀቹ 2020 የአሜሪካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጥሪ የደረሳት ሲሆን፥ አሜሪካ ኡዝቤኪስታንን ባሸነፈችበት ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ 90 ደቂቃ ተሰልፋ…
በለንደን ዳይመንድ ሊጉ ጉዳፍ ፀጋየ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በለንደን ዳይምንድ ሊጉ የ5 ሺህ ሜትር ወድድር አትሌት ጉዳፍ ፀጋየ ድል ቀንቷታል፡፡
ጉዳፍ ርቀቱን ለመጨረስ 14 ደቂቃ ከ12 ሴኮንድ የፈጀባት ሲሆን ተቀናቃኞቿን ሲፈን ሀሰን እና ብያትሪስ ቺቤትን በመቅድም ነው የ5 ሺህ ሜትር እርቀቱን በበላይነት ያጠናቀቀችው፡፡
በርቀቱ ኬንያዊቷ ብያትሪስ ቺቤት 2ተኛ እንዲሁም…