Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ሀዲያ ሆሳዕና ወላይታ ድቻን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ20ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎች በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂደዋል፡፡ በዚህም ሀዲያ ሆሳዕና ከወላይታ ድቻ ባደረጉት ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ተቀይሮ የገባው የአማካይ ተጫዋች መለሰ ሚሻሞ በ65ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ሀዲያ ሆሳዕና ወሳኝ ሶስት ነጥብ እንዲያገኝ አስችሎታል። ውጤቱንም ተከትሎ በሊጉ አምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ሀዲያ ሆሳዕና ነጥቡን ወደ 30 ከፍ አድርጓል። በአንጻሩ…
Read More...

አርባምንጭ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አርባምንጭ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና 1 አቻ ተለያዩ፡፡ ጎሎቹን ተመስገን ደረሰ ለአርባምንጭ ከተማ  እንዲሁም ሞሀመድ ናስር ለኢትዮጵያ ቡና አስቆጥረዋል፡፡ ክለቦቹ ነጥብ መጋራታቸውን ተከትሎ የደረጃ ለውጥ ሳያደርጉ በነበሩበት 12ኛ እና 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ በሌላ የጨዋታ…

ሳዲዮ ማኔ የ350 ሺህ ዩሮ የገንዘብ ቅጣት ተላለፈበት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የሊቨርፑል ኮከብ ሳዲዮ ማኔ የ350 ሺህ ዩሮ የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑን ክለቡ አስታውቋል፡፡ ማኔ የቡድን አጋሩን ሌሮይ ሳኔ በመልበሻ ክፍል ውስጥ በቡጢ በመደብደቡ ነው  የገንዘብ ቅጣቱ የተላለፈበት፡፡ የተጣለው የገንዘብ ቅጣትም በክለቡ ታሪክ ከፍተኛው መሆኑን  መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡…

በቦስተን ማራቶን አትሌት አማኔ በሪሶ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ቦስተን ማራቶን አትሌት አማኔ በሪሶ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች፡፡ አማኔ ርቀቱን 2 ሰዓት ከ21 ደቂቃ 50 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ሁለተኛ ደረጃን መያዝ የቻለችው፡፡ ርቀቱን ኬንያዊቷ አትሌት ሄለን ኦብሪ 2 ሰዓት ከ21 ደቂቃ 38 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት በበላይነት አጠናቅቃለች፡፡…

ሰሞኑን በተካሄዱ የአትሌቲክስ ውድድሮቸ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሣምንቱ መጨረሻ በተለያዩ ሀገራት በግል በተደረጉ የጎዳና ላይ ውድድሮቸ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በቻይና ውሃን ከተማ በተደረገ የጎዳና ላይ ውድድር  አትሌት ትዕግስት ታደሰ 2ኛ ሆና ስታጠናቀቅ÷ በዥንግ ካይ የወንዶች ማራቶን አትሌት ታፈረ አዲሱ፣ ገለታ ስንታዬሁ እና ወርቁ ድረሴ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ…

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ ድል ሲቀናው ኢትዮጵያ መድንና ወላይታ ዲቻ አቻ ተለያይተዋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ድል ሲቀናው ኢትዮጵያ መድንና ወላይታ ዲቻ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ በዛሬው ዕለት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡ በዚህም 9 ሰዓት ኢትዮጵያ መድንና ወላይታ ዲቻ ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን÷ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት…

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝነት በጋራ ስምምነት መለያየታቸው ተገለጸ፡፡ ተሰናባቹ አሰልጣኝ ከመስከረም 2013 ዓ.ም ጀምረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በዋና አሰልጣኝነት መርተዋል፡፡ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው÷ አሰልጣኝ ውበቱ ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ…