ስፓርት
በ18ኛው የዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ያስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን የጀግና አቀባበል ይደረግለታል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ያስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት አካባቢ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ይደረግለታል።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ዛሬም እንደ ትናንቱ፥ ፈተናዎችን በድል ተሻግረን፣ እጃችንን ለምስጋና እንዘረጋለን” በሚል መሪ ሀሳብ ባስተላለፉት መልዕክት፥ “የውስጥ ፈተናውንና የውጪ ጫናውን ተቋቁመው በዓለም የስፖርት መድረክ ላይ…
Read More...
ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ሽኝት ተደረገላቸው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በኮሎምቢያ ካሊ በሚደረገው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፉ አትሌቶች ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡
የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድኑ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማሪፊያ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተወካዮች በተገኙበት ሽኝት ተደርጎለታል፡፡
በኮሎምቢያ ካሊ የሚደረገው ከ20 ዓመት…
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ላሳዩት ሀገራዊ አንድነትና ላስገኙት ውጤት የጀግና አቀባበል ይደረግላቸዋል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላሳዩት ሀገራዊ አንድነትና ላስገኙት ወርቃማ ድል ልዩና ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግላቸው የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በአሜሪካ በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ነገ…
ሻምፒዮናውን ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛ ሆና አጠናቀቀች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (2014) የኦሪገንን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ አራት የወርቅ፣ አራት የብር እና ሁለት የነሃስ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች።
18ኛውን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከአፍሪካ በቀዳሚነት፣ ከዓለም ደግሞ ከአሜሪካ በመቀጠል 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።…
በሻምፒዮናው የመጠናቀቂያ ዕለት ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አልቀናቸውም
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (2014) በዛሬው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መጠናቀቂያ ዕለት በወንዶች 5 ሺህ ሜትር እና በሴቶች 800 ሜትር የፍፃሜ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አልቀናቸውም።
በወንዶች 5 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያው ወደ ኖርዌይ ሄዷል።
በውድድሩ ዩሚፍ ቀጀልቻ 8ኛ፣ ሰለሞን ባረጋ 12ኛ እና ሙክታር ኢድሪስ 13ኛ ሆነው አጠናቀዋል።…
በ18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ5000 ሜትር የወንዶች ፍጻሜ ውድድር ዛሬ ሌሊት ይደረጋል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በ18ኛው የኦሪገን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ5000 ሜትር የወንዶች ፍጻሜ ውድድር ዛሬ ሌሊት ይደረጋል።
ለሊት 10:05 በሚደረገው የወንዶች 5000 ሜትር ፍጻሜ ውድድር ላይ ሶስት ኢትዮጵያውን አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን፥ ሙክታር ኢድሪስ፣ ሰለሞን ባረጋ እና ዮሚፍ ቀጀልቻ የሚሳተፉ ይሆናል።
በተመሳሳይ ለሊት 10:35…
በኦሪገን ኢትዮጵያ በጉዳፍ ፀጋይ 4ኛዋን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሪገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶቾ 5 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ጉዳፍ ፀጋይ ለኢትዮጵያ 4ኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘች።
ዳዊት ስዩም ሶስተኛ በመውጣት የነሃስ ሜዳሊያ አስገኝታለች።
ውድድሩን ለተሰንበት ግደይ አምስተኛ በመውጣት አጠናቃለች።
በውድድሩ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ግሩም የቡድን ሩጫ አሳይተዋል።…