Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሴኔጋላዊው ሳዲዮ ማኔ የካፍ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ እግር ኳስ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የቀድሞው የሊቨርፑል ኮከብ እና የአሁኑ የባየር ሙኒክ አዲስ ፈራሚ ሳዲዮ ማኔ የካፍ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል፡፡ ሳዲዮ ማኔ በክለቡ ሊቨርፑል ማራኪ የውድድር ዓመት ከማሳለፉ በተጨማሪ÷ ሀገሩ ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን እንድትሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረጉ ነው የካፍ የ2022 ምርጥ ተጫዋች በመሆን የተመረጠው፡፡ በሞሮኮ ራባት በተካሄደው ምርጫ÷ ከሳዲዮ ማኔ በተጨማሪ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሊዮ ሲሴ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ሽልማትን…
Read More...

በወንዶች 5 ሺህ ሜትርና በሴቶች 800 ሜትር ስድስት ኢትዮጵያውያን ማጣሪያን አለፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወንዶች 5 ሺህ ሜትርና በሴቶች 800 ሜትር ስድስት ኢትዮጵያውያን ማጣሪያን አለፉ። የወንዶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ ከምድብ 1 አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ13:24.44 በሆነ ሰዓት 3ኛ ሆኖ በመግባት ቀጥታ ሲያልፍ አትሌት በ13:24.77 በሆነ ሰዓት 7ኛ የገባው አትሌት ጥላሁን ኃይሌ ማጣሪያውን አላለፈም። ከምድብ 2…

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሶስት ውድድሮች ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉበት የወንዶች 800 ሜትር ግማሽ ፍጻሜ ውድድር ንጋት 11 ሰአት ላይ ይካሄዳል፡፡ በ800 ሜትር የወንዶች ግማሽ ፍጻሜ ውድድር አትሌት ቶሎሳ ቦደና ይሳተፋል፡፡ ሌሊት 10 ሰዓት ከ10 ላይ በሚካሄደው የ5 ሺህ የማጣሪያ ውድድር÷ አትሌት ሰለሞን ባረጋ፣ አትሌት…

በ3 ሺህ የሴቶች መሰናክል ኢትዮጵያ የብርና ነሐስ ሜዳልያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ንጋት ላይ በተካሄደ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል የፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያ የብርና የነሐስ ሜዳሊያዎች አገኘች። አትሌት ወርቅውሃ ጌታቸው የብር እና መቅደስ አበበ የነሐስ ሜዳሊያዎችን አስገኝተዋል። የወርቅ ሜዳሊያውን የካዛኪስታን አትሌት አግኝታለች። የዛሬውን ውጤት ተከትሎ…

ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ለፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ ውድድር ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜው ውድድር አለፉ። በርቀቱ ኢትዮጵያን ወክለው ከተካፈሉት አትሌቶች ለተሰንበት ግደይ፣ ጉዳፍ ፀጋይ እና ዳዊት ስዩም ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል በወንዶች 800 ሜትር ማጣሪያ ቶለሳ ቦደና ወደ ቀጣይ…

ኢትዮጵያ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ፍፃሜ በሁለት አትሌቶች ትወከላለች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከንጋቱ 11 ሰዓት ከ45 ላይ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል የፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል፡፡ በፍጻሜው መቅደስ አበበ እና ወርቅውሃ ጌታቸው ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ። በሌላ በኩል ከሌሊቱ 8 ሰዓት ከ25 ላይ የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች የማጣሪያ ውድድር የሚካሄድ ሲሆን÷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ፣…

በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የደረጃ ሰንጠረዥ ኢትዮጵያ 2ኛ ላይ ተቀምጣለች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ኦሬጎን እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የደረጃ ሰንጠረዥ ኢትዮጵያ 2ኛ ስፍራን ይዛለች፡፡   በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ እስካሁን ሶስት የወርቅ እና ሶስት የብር ሜዳሊያ በማምጣት ነው ከአሜሪካ ቀጥላ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው፡፡   በሴቶች 10 ሺህ ሜትር…