በፕሪሚየር ሊጉ ሀዲያ ሆሳዕና ወላይታ ዲቻን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዲያ ሆሳዕና ወላይታ ዲቻን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
5ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ጨዋታ ዛሬ 7 ሰዓት በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
በጨዋታው ሀዲያ ሆሳዕና ወላይታ ዲቻን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የማሸነፊያ ግቡን በ68ኛ ደቂቃ ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን አስቆጥሯል፡፡