ስፓርት
የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር የመልስ ጨዋታውን ያካሂዳል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴቶች ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሦስተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ ዛሬ ደቡብ አፍሪካን ትገጥማለች፡፡
ጨዋታው÷ ዛሬ 10፡00 ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚካሄድ ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የመጀመሪያው ጨዋታ ጆሃንስበርግ ላይ ተካሂዶ ኢትዮጵያ 3 ለ0 ማሸነፏ ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-…
Read More...
በጀርመን በተካሄደ የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲዳስ ኩባንያ 'adizero' በሚል በጀርመን ባዘጋጀው የ5 ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ አሸንፈዋል።
በጀርመን በተካሄደ የ5 ኪሎሜትር ሩጫ ውድድር በሴቶች÷ አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ 14 ደቂቃ 37 ሰከንድ 2 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ነው ውድድሩን በበላይነት…
በፕሪሚየር ሊጉ ጅማ አባ ጅፋር ከሰባት ጨዋታዎች በኋላ ድል አስመዝግቧል
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ21ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።
ቀደም ብሎ በተካሄደ ጨዋታ ጅማ አባ ጅፋር ከባህር ዳር ከተማ ተገናኝተዋል።
ጨዋታውን ጅባ አባ ጅፋር 2 ለ 0 ሲያሸንፍ አስጨናቂ ፀጋዬ እና ሱራፌል አወል የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ጅማ አባ ጅፋር…
የፕሪሚየር ሊጉ የዲስፕሊን ኮሚቴ በባሕር ዳር ከተማው አጥቂ ሁሴን ማውሊ የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዲስፕሊን ኮሚቴ በባሕር ዳር ከተማው አጥቂ ሁሴን ማውሊ ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
የሊጉ የዲስፕሊን ኮሚቴ የ21ኛ ሣምንት መርሐ ግብር ከመጀመሩ በፊት በሣምንቱ በተከሰቱ የዲስፕሊን ግድፈቶች ላይ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
በዚሁ መሰረት መከላከያ ከባሕር ዳር ከነማ…
ጅማ አባ ጅፋር አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን ከስራ አገደ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ጅማ አባጅፋር አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን ከስራ ማገዱ ተገልጿል፡፡
የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ ጅማ አባ ጅፋር ያለፉትን አመታት በተለያዩ ጫናዎች ውስጥ ሆኖ ላለመውረድ ሲጫዎት ቆይቷል፡፡
ከነበረበት ጫና ለመውጣት በዘንድሮው የውድድር አመት አሰልጣኝ…
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ድል ቀናው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ20ኛ ሣምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ዛሬ በተደረገ ጨዋታ ፋሲል ከነማ አርባ ምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በአዳማ ሣይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ በተደረገው ጨዋታ÷ ፋሲል ከነማ በበዛብህ መለዮ ድንቅ ጎል አርባምንጭ ከተማን በማሸነፍ ወሳኝ 3 ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል፡፡…
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዲስ አበባ ከአዳማ ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 17፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ20ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዲስ አበባ ከተማ ከአዳማ ከተማ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች ጨዋታቸውን ያለ ግብ አጠናቀዋል፡፡
የጨዋታውን ውጤት ተከትሎ አዳማ ሃዲያ ሆሳናን…