ስፓርት
በሐዋሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 4ኛው የመላ ኢትዮጵያ ሴቶች ጨዋታ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከሚያዝያ 1 እስከ 9 ቀን 2014 ዓ.ም "የሴቶች እኩል ተሳታፊነት ለስፖርት ውጤታማነት" በሚል መሪ ቃል ለአንድ ሳምንት ሲካሄድ የቆየው 4ኛው የመላ ሴቶች ጨዋታ ተጠናቋል።
ኦሮሚያን ከሲዳማ ባገናኘው የፍጻሜ የእግር ኳስ ጨዋታ ኦሮሚያ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸናፊ ሆኗል፡፡ በዚህም ኦሮሚያ የወርቅ፣ ሲዳማ የብር፣ አዲስ አበባ የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
በባህል ስፖርቶች ውድድር ኦሮሚያ 1ኛ፣ ሲዳማ 2ኛ እና አዲስ አበባ…
Read More...
በፕሪሚየርሊጉ ሳላዲን ሐት ትሪክ ሲሰራ ቅዱስ ጊዮርጊስ አቻ ተለያይቷል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።
ቀደም ብሎ በተካሄደ ጨዋታ መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ ያለምንም ጎል አቻ ተለያይቷል።
ማምሻውን በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ ሰበታ ከተማ ከሲዳማ ቡና ተገናኝተዋል።
ጨዋታው በሲዳማ ቡና 3 ለ 0 አሸናፊነት ሲጠናቀቅ…
17ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን የበላይነት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 17ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን የበላይነት ተጠናቀቀ፡፡
በጂግጂጋ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 17ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር ፍፃሜውን አግኝቷል።
በውድድሩ÷ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን አንደኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን÷ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለተኛ…
የ2022 ካዛኪስታን – ዱሻንቤ ኢንተርናሽናል ግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2022 ካዛኪስታን - ዱሻንቤ ኢንተርናሽናል ግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በሴቶች አትሌት በቀሉ አበበ የ2022 ካዛኪስታን - ዱሻንቤ ኢንተርናሽናል ግማሽ ማራቶን ውድድር አሸናፊ ሆናለች፡፡
በተመሳሳይ መርሐ ግብር በወንዶች አትሌት ግርማ ጥላሁን ሁለተኛ ደረጃን…
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የደቡብ አፍሪካ አቻውን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የደቡብ አፍሪካ አቻውን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ቡድኑ ዛሬ በሴቶች ዓለም ዋንጫ ማጣርያ 3ኛ ዙር ጨዋታውን ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር አካሂዷል፡፡
በደቡብ አፍሪካ ዊትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች…
በ2014 የኢትዮጵያ ውኃ ዋና ሻምፒዮን የአማራ ክልል አሸናፊ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በኢትዮጵያ ውኃ ዋና ሻምፒዮን አማራ ክልል በሁለቱም ፆታ አሸናፊ ሆኗል።
በቢሾፍቱ ከተማ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የነበረው የ2014 የኢትዮጵያ ውኃ ዋና ሻምፒዮን ዛሬ ተጠናቋል።
የአማራ ክልል በሁለቱም ፆታ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኖ ሁለቱንም ዋንጫዎች ሲወስድ ክልሉ ለስፖርቱ ባበረከተው አስተዋፅኦ ልዩ የዋንጫ…
በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ፋሲል ከነማ ወደ አሸነፊነት የተመለሰበትን ውጤት አስመዝግቧል፡፡
ፋሲል ከነማን ከጅማ አባ ጅፋር ያገናኘው ጨዋታ በፋሲል ከነማ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ጅማ አባ ጅፋር ሙሃመድ ኑር ናስር ባስቆጠራት ጎል እስከ እረፍት ሲመራ ቢቆይም ከእረፍት መልስ ይሁን እንዳሻው…