Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ፍሬወይኒ ኃይሉ በሴቶች የ1500 ሜትር ለፍጻሜ አለፈች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በሴቶች የ1 ሺህ 500 ሜትር ለፍጻሜ አልፋለች፡፡ በ1 ሺህ 500 ሜትር በምድብ አንድ የግማሽ ፍፃሜ ውድድሯን ያደረገችው አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በ3 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ54 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት 2ኛ በመውጣት ወደ ፍፃሜ ማለፏን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። አትሌት ለምለም ሀይሉ 9ኛ በመሆን ለፍፃሜ ሳትደርስ ቀርታለች ፡፡ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦…
Read More...

ዛሬ ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉባቸው የፍጻሜ እና የማጣሪያ ውድድሮች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ዛሬ በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይሳተፋሉ፡፡ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት በሴቶች 1500 ሜትር ማጣሪያ ለግማሽ ፍፃሜ ያለፉት ፍሬወይኒ ገ/እግዚአብሄር እና ለምለም ሀይሉ ለፍፃሜ ለማለፍ ይወዳደራሉ፡፡ በተጨማሪም 8:00 ሰዓት ላይ በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል የፍፃሜ ውድድር መቅደስ አበበ እና ዘርፌ…

በቶኪዮ ኦሊምፒክ በ800 ሜትር ሴቶች ውድድር የተሳተፈችው አትሌት ሀብታም አለሙ 6ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ በ800 ሜትር ሴቶች ውድድር የተሳተፈችው አትሌት ሀብታም አለሙ 6ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቃለች፡፡ በዚህም የዲፕሎማ ተሸላሚ ሆናለች፡፡ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡-…

በ5000 ሜትር ወንዶች አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ ለፍፃሜ አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በ5000 ሜትር ወንዶች አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ ለፍፃሜ አልፏል፡፡ እየተካሄደ ባለው የቶኪዮ ኦሎምፒክ በሁለት ምድብ ተካፍሎ በተካሄደው የ5000 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ውድድር ላይ ከተካፈሉት አትሌቶች መካከል አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ ሲያልፍ÷ አትሌት ጌትነት ዋለ እና አትሌት ንብረት መላክ ሳያልፉ ቀርተዋል፡፡ አትሌት ሚልኬሳ…

በቶኪዮ ኦሎምፒክ ዛሬ የሚጠበቁ የፍፃሜ እና የማጣሪያ ውድድሮች

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በቶኪዮ ኦሎምፒክ ዛሬ ከሰዓት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይጠበቃሉ፡፡ ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረገው የ5000 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ውድድር እንዲሁም ከቀኑ 9፡25 ላይ በሚደረገው የ800 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይወዳደራሉ፡፡ በ800 ሜትር ኢትዮጵያን ወክላ ሃብታም አለሙ ትሮጣለች፡፡…

የ2014 የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2014 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡ በዚህ መሰረት አርባ ምንጭ ከተማ ከመከላከያ፣ ባህር ዳር ከተማ ከአዲስ አበባ ከተማ ይጫወታሉ፡፡ በሌላ በኩል ፋሲል ከነማ ከሀዲያ ሆሳዕና፣ አዳማ ከተማ ከወልቂጤ ከተማ፣ ሀዋሳ ከተማ ከጅማ አባጅፋር የሚገናኙ…

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በተገኙ ተጨማሪ ውጤቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በዛሬው እለት በተገኙ ተጨማሪ ውጤቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡ ፕሬዚዳንቷ “የኢትዮጵያ ልጆች አትሌት ለሜቻ ግርማ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የብር እንዲሁም በሴቶች አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ በ5 ሺህ ሜትር የነሃስ ሜዳልያዎች ባለቤት አድርገውናል”…