ስፓርት
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በቶኪዮ ፓራ ኦሊምፒክ ለሚሳተፈው ልዑክ ሽኝት አደረጉ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በቶኪዮ ፓራ ኦሊምፒክ ተሳትፎ አስፈላጊውን መመዘኛ ላሟሉ የኢትዮጵያ ቡድን አባላት ሽኝት አደረጉ።
ፕሬዚዳንቷ የአካል ጉዳተኛ መሆን ማነስ ያለመሆኑን ጠቅሰው የሀገራቸው ሰንደቅ አላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደርጉ ዘንድ መልካሙን ተመኝተውላቸዋል።
ኢትዮጵያ በፓራ ኦሊምፒክ ውድድር መሳተፍ የሚችሉ በርካታ ዜጎች እንዳሏት የጠቀሱት ተወዳዳሪዎቹ መመዘኛውን ለማሟላት በሚደረገው ጥረት የሚመለከታቸው ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
የእነርሱ ተሳትፎ…
Read More...
በቶኪዮ የፓራኦሊምፒክ ጨዋታዎች ተመልካቾች በስቴዲየም አይታደሙም
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓን ቶኪዮ የፓራ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ያለ ተመልካች እንደሚካሄዱ አስተባባሪዎች አስታወቁ።
ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት መጨመር ጋር ተያይዞ ቫይረሱን ለመቆጣጠር ጃፓን ከፍተኛ ችግር ውስጥ በመውደቋ ተመልካቾች ጨዋታዎችን በአካል ተገኝተው አይታደሙም ተብሏል።
የጨዋታዎቹ አስተባባሪዎች ደጋፊዎች በየጎዳናው ጨዋታዎችን ተሰባስበው…
ለአትሌቶች እና አሰልጣኞች ሽልማት ተበረከተ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ክልል መንግስት በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ሜዳልያ ላስገኙ አራቱ አትሌቶች እና አሰልጣኞች ማበረታቻ ሽልማት አበረከተ ።
ለሰለሞን ባረጋ 500ሺህ ብር፣ 10ሺህ ካሬሜትር በወልቂጤ ከተማ የኢንቨስትመንት ቦታ እንዲሁም የማዕረግ እድገት ተሰጥቶታል፡፡
ለአትሌት ለሜቻ ግርማ 350 ሺህ ብር፣ ለአትሌት ለተሰንበት…
ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚሆን ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በደቡብ ክልል ሊካሄድ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመንግሥትና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚሆን ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በደቡብ ክልል እንደሚከናወን ተገለፀ።
የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ የሺዋስ አለሙ ፥ መንግስት በትግራይ ክልል ህግን ለማስከበር እያደረገ ላለው ተግባር ለመንግሥትና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚሆን ማህበረሰብ አቀፍ…
በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን አቀባበል ተደረገለት
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ዛሬ ጠዋት አቀባበል ተደርጎለታል::
ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው አቀባበል የተደረገለት ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦…
ብራዚል በቶኪዮ ኦሊምፒክ የወንዶች እግር ኳስ አሸናፊ ሆነች
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚል በቶኪዮ ኦሊምፒክ የወንዶች እግር ኳስ አሸናፊ ሆነች።
በፍጻሜው ከስፔን ጋር የተገናኘችው ብራዚል ጨዋታውን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አንድ አቻ የተጠናቀቀ ሲሆን፥ በተጨማሪ 30 ደቂቃዎች ብራዚል ተጨማሪ ጎል አስቆጥራ የውድድሩ አሸናፊ ሆናለች።
ለብራዚል የድል ጎሎቹን…
ጠ/ሚ ዐቢይ በአትሌት ለተሰንበት ግደይ በተመዘገበው ውጤት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር በአትሌት ለተሰንበት ግደይ የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘቷ የእንኳን ደስ አለን መልዕክት አስተላለፉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ለወንዶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻች መልካም ዕድል ተመኝተዋል፡፡…