ስፓርት
አሰልጣኝ ዘማሪያም ወ/ጊዮርጊስ የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ሆኑ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ዘማሪያም ወልደጊዮርጊስ የድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ በመሆን በይፋ ክለቡን መረከባቸው ተነገረ፡፡
አሰልጣኙ ከዚህ በፊት የወልዋሎ አዲግራት እግር ኳስ ክለብን ጨምሮ አዳማ ከተማ፣ ፋሲል ከነማ፣ ወልድያ ከተማ እና ጅማ አባ ጅፋርን ማሰልጠናቸው ይታወሳል፡፡
አሁን ደግሞ በአንድ አመት ውል ድሬዳዋ ከተማን መቀላቀላቸው ታውቋል፡፡
ቡድኑን ወደተሻለ ደረጃ ማድረስም የቤት ስራቸው እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን ስራቸውን ደግሞ የፊታችን ሐሙስ ሐዋሳ ከተማን…
Read More...
አትሌት ሰምበሬ ተፈሪ በድሬዳዋ በተካሄደው 14ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ማረሚያ ቤትን በመወከል የተወዳደረችውአትሌት ሰምበሬ ተፈሪ በድሬዳዋ በተካሄደው 14ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር አሸንፋለች፡፡
ዓለም አቀፍ ዝና ያላቸው ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተሣተፉበትና ዛሬ በድሬዳዋ ከተማ በተካሄደው ግማሽ ማራቶን ውድድር በኦሮሚያ ክልልና በኦሮሚያ ፖሊስ ክለብ የበላይነት ተጠናቋል፡፡…
ፋሲል ከነማ ሃዋሳ ከተማን በማሸነፍ የፕሪምየር ሊጉን መሪነት አጠናከረ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ሃዋሳ ከተማን 2ለ 1 አሸነፏል፡፡
የፋሲል ከነማን ሁለት ግቦች በረከት ደስታ እና አምሳሉ ጥላሁን አስቆጥሯል፡፡
የሃዋሳ ከተማን ብቸኛ ግብ ወንድማገኝ ኃይሉ በ70ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
ጠዋት በተካሄደ ጨዋታ ጅማ አባ ጅፋር ሲዳማ ቡናን 1ለ…
ጅማ አባ ጅፋር ሲዳማ ቡናን አሸነፈ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጅማ አባ ጅፋር ሲዳማ ቡናን 1ለ 0 አሸነፈ፡፡
ሱራፌል አወል ለጅማ አባ ጅፋር ብቻኛዋን ጎል አስቆጥሯል፡፡
ዛሬ 9 ሰዓት ሃዋሳ ከተማ እና ፋሲል ከተማ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦…
14ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በድሬደዋ ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በድሬደዋ ከተማ ለ14ኛ ጊዜ ተካሄደ።
የሴቶች ውድድር ከማለዳው 1:30፣ የወንዶችም ደግሞ 1:45 ጀምሮ ተካሂዷል።
የሴቶችን ውድድር የድሬደዋ ምክትል ከንቲባ ከድር ጁሃር እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ሣራ ሃሰን፤ የወንዶቹን ውድድር ደግሞ…
ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳማ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳማ ከተማን 4 ለ 2 አሸነፈ፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ጎሎች አቤል እንዳለ በ12ኛው፣ ጌታነህ ከበደ በ32ኛው፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል በ59ኛው እና በ88ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡
የአዳማ ከተማን…
ሰበታ ከተማ ወልቂጤን 1 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ12ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰበታ ከተማ ድል ቀንቶታል፡፡
9 ሰአት ላይ በተደረገው ጨዋታ ሰበታ ከተማ ወልቂጤ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ፍጹም ገብረማርያም ደግሞ የድል ጎሏን አስቆጥሯል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦…