Fana: At a Speed of Life!

ዩኒቨርሲቲው የህፃናትን ሞት ለመቀነሰ የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የህፃናትን ሞት ለመቀነሰ 5 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚገመት የተለያዩ ድጋፎችን አድርጓል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከ 5 ዓመት በታች ዕድሜ ያላቸው ህፃናትን ሞት አሁን ከሚገኝበት ደረጃ ለመቀነሰ ‘ቻመፐሰ’ በተሰኘው ፕሮጀክት አማካኝነት በምሰራቅ ሐረርጌ ዞን የተለያዩ ሰራዎች እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

ለሰራዎች እንዲያግዘም 5ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ወጭ ተደርጎበት ለአካባቢው ጤና ተቋማት የተለያዩ የቁሳቁሰ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

22 የአልትራሳውንድ ማሽኖች ፣ 48 ፍራሾች ፣ 51 አልጋዎች እያንዳንዳቻው ፣ 20 የሺህ ብር ዋጋ ያላቸው 36 የሙቀት መለኪያ እና ሌሎች መሰል ድጋፎችም ተደርጓል፡፡

በድጋፉ ስነ-ሰርዓት ላይ የተገኙት የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶክተር ጀማል ዩሱፍ ÷ የህፃናትን ሞት ለመቀነሰ ፕሮጀክቱ እየሰራ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን በማንሳት ይህን መሰል ድጋፎች በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

በነስሪ ዩሱፍ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.