Fana: At a Speed of Life!

ጃማ፣ ወረኢሉና ኩታበር ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃማ፣ ወረኢሉና ኩታበር ከተሞች ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ከህወሓት ወረራ ነፃ የሆኑ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል በፍጥነት እንዲያገኙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን የሚጠግንና የሚገነባ ቡድን በማቋቋም ወደ ስራ የገባው የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት የከተሞችን ኤሌክትሪክ መልሶ በማገናኘት ላይ ይገኛል፡፡

በዚህም በዛሬው ዕለት ወራሪው ቡድን ወደ ደቡብ ወሎ ዞን ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ኤሌክትሪክ ተቋርጦባቸው የነበሩት ጃማ፣ ወረኢሉና ኩታበር ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የሀይቅና ቢስቲማ ከተሞች የዝቅተኛና የመካከለኛ መስመር ጥገናም እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ የደሴ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሀብቱ አበበ ገልፀዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.