የምርጫ ሂደቱ ግልጽ እና ፍትሐዊ ነው – ታዛቢዎች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ቃሉ 1 ምርጫ ክልል እየተካሄደ ያለው ምርጫ ፍትሐዊ፣ ግልጽ እና የምርጫ ሕጉን የተከተለ ነው አሉ የምርጫ ታዛቢዎች።
በሁርባ ቀበሌ 2 ምርጫ ጣቢያ ጤና ኬላ 2ሀ የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ታዛቢ ሙሐመድ እንድሪስ እንዳሉት÷ ምርጫው እስከ አሁን ድረስ ምንም ዓይነት ጣልቃ ገብነት ሳይታይበት ፍትሐዊ በሆነ መልኩ እየተካሄደ ነው።
በአሰን ሀገር ክፍለ ከተማ ሁዳድ ቀበሌ ሚሊኒየም ምርጫ ጣቢያ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ታዛቢ ሱልጣን ኢብራሂም በበኩላቸው÷ የምርጫ ሂደቱ ያለምንም ጫና ተካሂዷል ብለዋል።
በዚሁ ጣቢያ የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ታዛቢ አራጋው ሁሴን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ሕጉን በተከተለ መልኩ እንደቀጠለ ገልጸዋል።
ሕዝቡ በነጻነት ድምጹን እየሰጠ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በአቢሽ ሀገር፣ ቀዲዳ ቀበሌ ምርጫ ጣቢያ የብልጽግና ፓርቲ ታዛቢ ሰይድ ጀማል ናቸው።
የወጣቶች ማሕበር ተወካይ ወጣት ሙሐመድ ሐሰን እንዳሉት÷ የምርጫ ሂደቱ ፍጹም ነፃ በሆነ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል።
በሙሉቀን አበበ
#ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያእየመረጠችነው #በምርጫብቻ #ፋናዲጂታል #Election #fanadigital #Ethiopia #Ethiopiavotes #Democracy #fanatelevision