ለአገር ክብር እየተደረገ ያለው ተጋድሎ ዳግማዊ አድዋን ለማስመዝገብ የተዘጋጀ ትውልድ መኖሩን ማሳያ ነው – የኦሮሚያና የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ክብር ለማስጠበቅ እየተደረገ ያለው ተጋድሎ ዳግማዊ አድዋን ለማስመዝገብ የተዘጋጀ ትውልድ መኖሩን ማሳያ ነው ሲሉ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ የኦሮሚያና የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ገለጹ፡፡
አሸባሪው ቡድን አላማ ያደረገው ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ደቃ ህዝቦቿ እንዲበታተኑ ማድረግ ነው የሚሉት የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ሃላፊ ቀለመወርቅ ምህረቴ፥ ቡድኑ ባለፉት አመታት የተወሰኑት አካላት የሚበለጽጉበትን እና የተወሰኑት ደግሞ የሚደኸዩበትን መንገድ ሲያከናውን እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡
አሸባሪው ቡድን በግለሰብ ቤት የውድመት እና የዘረፋ ስራ ከመስራት ጀምሮ መንግስታዊ የሆኑ ተቋማት ንብረቶችን ዘርፎ ወስዷል ቀሪዎችንም ለስራ እንዳይውሉ አድርጎ አውድሟልም ነው ያሉት፡፡
በኢኮኖሚው መስክ የሚሳተፉ አካላት ችግር ውስጥ እንዲቆዩ ለማድረግ፥ የክልል ብሎም የአገር ኢኮኖሚ እንዲናጋ ስራ ሰርቷልም ብለዋል ሃላፊው፡፡
በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የመንግስት ሀብት አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር ግርማ አመንቴ በበኩላቸው፥ የምግብ ፍጆታን በአገር ውስጥ ምርት መሸፈን በአገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያው ትልቅ ትኩረት እንደተሰጠው ይናገራሉ።
በአገር ውስጥና በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት ያለው ተጋድሎ ትልቅ ነው ያሉት ዶክተር ግርማ፥ በሁሉም ግንባሮች ተጋድሎ አድርገን ማሸነፍ አለብን ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያን ክብር ለማስጠበቅ እየተደረገ ያለው ተጋድሎ ዳግማዊ አድዋን ለማስመዝገብ የተዘጋጀ ትውልድ መኖሩን ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ ቀያቸው ከመመለስ እና የወደሙ የግልም ሆነ የመንግስት ተቋማትን ወደ አገልግሎት ከመመለስ አንጻር ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግም አንስተዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!