Fana: At a Speed of Life!

ኬንያ በሁሉም ወቅት ለኢትዮጵያ ያላት አጋርነት የማይዋዥቅ ነው – ጄኔራል ባዲ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የናይሮቢ የሜትሮፖሊታን አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል ሌተናት ጄነራል መሀመድ አብደላ ባዲ በኢትዮጵያ እና ኬንያ መካከል ያለው ግንኙነት በመንግስታት መቀያየር የማይዋዠቅ መሆኑን ገለፁ፡፡

ጄነራል ባዲ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ ዓለም በጽህፈት ቤታቸው በተቀበሉበት ወቅት የሁለቱ አገራት ግንኙነት በጋራ ህዝቦች አንድነት በፅኑ መሠረት ላይ የቆመ ከቀድሞዎች አባቶቻችን የወረስነው እንጂ እኛ የፈጠርነው አይደለም ብለዋል፡፡

ኬንያ በሁሉም ወቅት ለኢትዮጵያ ያላት አጋርነት የማይዋዥቅ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

የናይሮቢ ከተማ በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩበት ነው ያሉት ዳይሬክተር ጄነራሉ ፥ የናይሮቢ ከተማ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር መተሳሰር እንደምትፈልግ ገልፀዋል፡፡

የናይሮቢ ከተማ አዲስ የሚያሰራውን ፓርክ በተመለከተ ከእንጦጦ እና አንድነት ፓርክ ልምድ መቅሰማቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

አምባሳደር መለስ ዓለም በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ÷ የኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት እንዲረጋገጥ የኬንያ ኘሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ለሰጡት ድጋፍ እንዲሁም ኬንያዉያን ላሳዩት አጋርነት ምስጋና ማቅረባቸውን በኬኒያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.