ከጃማ ደጎሎ እስከ አለም ከተማ ያሉ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ሃይል አገኙ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት የነበረው ከጃማ ደጎሎ እስከ ዓለም ከተማ ያለው ከፍተኛ ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቆ አካባቢዎቹ ኃይል ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎችና ማስተላለፊያ መስመሮች ኦፕሬሽን ዘርፍ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ውቤ ÷ ከአንድ ወር በላይ ኃይል ተቋርጦባቸው የነበሩት የሚዳ መራኛ፣ ዓለም ከተማ፣ ፌጥራ፣ ሬማ፣ ደራ ጉንዶመስቀል እና ለሚ ከተሞች ከቀኑ 6 ሰዓት ሰዓት ጀምሮ ኃይል እንዳገኙ መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!