የአሸባሪ ቡድኑን እኩይ ተግባር የሚያወግዙ ሰልፎች በሀረር፣ ደብረማርቆስ፣ ዲላና ሳውላ፣ ጋምቤላና አሶሳ ከተሞች ተካሄዱ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪ ቡድኑን ህወሃት እኩይ ተግባር የሚያወግዙ እና አሜሪካና አንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያለውን ጣልቃ ገብነት የሚያወግዙ ሰልፎች በሀረር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ዲላና ፣ ሳውላ፣ ጋምቤላ እና አሶሳ ከተሞች ተካሄዱ፡፡
የሀረሪ ክልል ሴቶች አሸባሪው ህወሓት በወረራ ይዞቸው በነበሩ አካባቢዎች በሴቶች እና ህፃናት ላይ ያደረሰውን ጥቃት በማውገዝ “ለእህቴ ጠበቃ ነኝ፤ ልጄ ጥቃት ሲደርስባት ዝም አልልም፤ መሪዬ ሲዘምት ለኢትዮጵያ እኔ አለሁላት” የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡
አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሴቶችና ህፃናትን መድፈሩ እንዲሁም የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲል ህፃናቱን ወደ ጦርነት መማገዱ እንዳስቆጣቸው የተናገሩት ሴት ሠልፈኞቹ፥ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪው ቡድን እያደረሰ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት አይተው አንዳላየ ማለፋቸው እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል፡፡
በሌሎቹ ከተሞች በተደረጉት ሰልፎች ‘‘ጀግኖቻችን እኛ እስክንደርስ ኢትዮጵያን አደራ፣ ጀግኖቻችን ለእኛ ስትሉ አንድ ህይወታችሁን ሰጥታችሗል፣ የእኛ ትውልድ ደግሞ ታሪካችሁን የመጠበቅ አደራ አለበትና ቃላችን አይታጠፍም ” የሚሉ መልዕክቶችን አሰምተዋል፡፡
‘‘የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን በግምባር እየተዋደቀ ህይወቱን ሰውቶ ሀገር ለማቆየት የሚከፍለዉ መሰዋትነት በምንም የሚተመን አይደለምና ሁሌም ከጎኑ በመቆም ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለንም” ብለዋል ሰልፈኞቹ፡፡
አሸባሪው ህወሓትና የጥፋት ተላላኪዎቹ ህጻናትን ጨምሮ በሴቶች ላይ የሚፈጽሙትን ፆታዊ ጥቃትና የንጹሃን ጭፍጨፋ የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
አሸባሪው ህወሓት በአማራና አፋር ክልሎች ሴቶችን በመድፈርና ንጹሃን ዜጎችን በግፍ በመጨፍጨፍ በፈጸመው አስከፊ ወንጀል በአለም አቀፍ ህግ ሊጠየቅ ይገባል ፤ ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉት ጫና ያቁሙ የሚሉ መልዕክቶችን ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በተመሳሳይ ወራሪው ቡድን በሴቶች እና ህፃናት ላይ እየደረሰ ያለውን ዘግናኝ ግፍ የሚቃወም እንዲሁም አሜሪካ እና ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያለውን ጣልቃ-ገብነት የሚያወግዝ የተቃውሞ ሠልፍ በአሶሳ ከተማ ተካሄደ፡፡
በሰልፉ ላይ ‘‘ሠላም ይስፈን በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም ፤ የሴቶች ጥቃትን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀም ይብቃ ፤ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ድርጅቶች የተዛባ ዘገባቸውን ያቁሙል ፤ በአሸባሪው ቡድን የሚደርሱ የሴቶችና የህፃናት ጥቃትን በጥብቅ እናወግዛለን’’ የሚሉና የተለያዩ መልዕክቶችም በሰልፉ ላይ ማንጸባረቃቸውን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በቲያ ኑሬ፣ ታሪክነሽ ሴታ እና ማቴዎስ ፈለቀ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!