Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ መመሪያ የውጭ ምንዛሬ እንዳይባክንና ተጠያቂነትን ለማስፈን ያስችላል- የዘርፉ ምሁር

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬን በተመለከተ በቅርቡ ያወጣው መመሪያ የውጭ ምንዛሬ እንዳይባክንና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያስችል መሆኑን የዘርፉ ምሁር ጠቆሙ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ አጠቃቀምን በተመለከተ በቅርቡ ያወጣው መመሪያ አዳዲስ አሰራሮችን ይዞ መጥቷል ነው ያሉት ምሁራኑ።
ባንኮች ከሚያቀርቧቸው የውጭ ምንዛሬ አገልግሎቶች 50 በመቶ የሚሆነው መንግሥት ትኩረት ባደረገባቸው ፕሮጀክቶች ላይ መዋል እንዳለባቸው መመሪያው ያስገድዳል።
ቀሪውን ባንኮቹ ለፈለጓቸው የሥራ መስኮች ማዋል የሚችሉ ሲሆን፥ ያልተጠቀሙበትን የውጭ ምንዛሬ ደግሞ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረግ እንዳለባቸው ደንግጓል።
በመመሪያው መሰረት የውጭ ምንዛሬ ቅድሚያ ማግኘት ካለባቸው ሴክተሮች መካከል በመጀመሪያ ደረጃ የፋርማስዩቲካልና የምግብ ዘይት ግብዓቶች እና ነዳጅ ይገኙበታል።
በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ለግብርና ለአምራች ኢንደስትሪዎች ግብዓትነት ግዥ የሚውሉ የውጭ ምንዛሬዎች መፈቀድ እንዳለበት መመሪያው አቅጣጫ አስቀምጧል።
በሦስተኛ ደረጃ የሞተር ዘይትን ጨምሮ በርካታ ለሕክምና ላብራቶሪ፣ ለግብርና፣ ለትምህርት፣ ለአምራች ዘርፍና ሌሎችም ሴክተሮች ትኩረት መደረግ እንዳለበት አመላክቷል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ንግድ ሥራ ኮሌጅ የኢኮኖሚክስ መምህሩ ዶክተር ብርሃኑ ደኑ ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ መመሪያው የውጭ ምንዛሬን በአግባቡ ለመጠቀም ያስችላል።
በአሁኑ ጊዜ ያለውን ውስን የውጭ ምንዛሬ ሀብት ከብክነት ለመከላከልና ፍሰቱንም ለመቆጣጠር አመቺ መመሪያ ነው ብለዋል ዶክተር ብርሃኑ።
በተጓዳኝም የውጭ ምንዛሬ ሕገ-ወጥ በሆነ መልኩ ከአገር እንዳይወጣና ጠቃሚ ባልሆነ ዘርፍ ላይ እንዳይውል ለማድረግም ይረዳል ነው ያሉት።
በተለይም የምግብ ዘይት አማራቾች በመጀመሪያ ደረጃ የውጭ ምንዛሬ እንዲያገኙ መደረጉ፥ ዘርፎቹ ምርትና ምርታማነታቸውን በማስፋት ከውጭ ተመሳሳይ ምርት ለማስገባት የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ ማዳን እንደሚያስችልና ይህም ትልቅ እመርታ መሆኑን ጠቁመዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.