Fana: At a Speed of Life!

የአልወሃ ድልድይ በአሸባሪው ህወሃት ፈርሷል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ከወልዲያ ወደ ቆቦ የሚወስደው የአልወሃ ድልድይ በአሸባሪው ህወሃት ፈርሷል።
 
አሸባሪው ህወሃት በገባባቸው አካባቢዎች ሁሉ መሰረተ ልማቶችንና የህዝብ መገልገያዎችን መዝረፍና ማውደም ዋነኛ ዓላማው አድርጎ ተንቀሳቅሷል።
 
የሽብር ቡድኑ አሁን ላይ በፀጥታ ሃይሎች የጋራ ክንድ እየደረሰበት ያለውን ከፍተኛ ምት መቋቋም ባለመቻሉ በሽሽትም ላይ ሆኖ መሰረተ ልማቶችን እያወደመ ይገኛል።
 
ከትናንት በፊት በሀይቅና ውጫሌ ከተሞች መካከል ያለውን ድልድይ አፍርሶ ከፈረጠጠ በኋላ ዛሬ ሌሊት ደግሞ በጣሊያን ጊዜ የተሰራውን ጥንታዊውን የአልወሃ ድልድይ አፍርሶ መሸሹን ኢዜአ ዘግቧል።
 
የሽብር ቡድኑ ይሄንን ውድመት ያደረሰው የመሰረተ ልማት አውታሮችና ተቋማትን የማፍረስ እኩይ ዓላማውን ለማሳካት እንዲሁም ከጸጥታ ሃይሉ የፈጣን እንቅስቃሴ ጥቃት ለመትረፍ በማሰብ መሆኑ ታውቋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.