በወልዲያ 5 ለፍቶ አዳሪዎች እንዲንበረከኩ ተደርጎ በጥይት እሩምታ ተጨፍጭፈዋል
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በወልዲያ ከተማ ውሃ ለመቅዳት ወንዝ የወረዱ አምስት ለፍቶ አዳሪዎችን በሰልፍ እንዲንበረከኩ በማድረግ በጥይት እሩምታ ጨፍጭፏል።
የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች የጨለማ ጊዜ ያሳለፉት በመብራት እጦት ብቻ ሳይሆን በሚደርስባቸው መከራና ግፍ ጭምር ነበር።
የከተማዋ ነዋሪ የሆነችው የአይን እማኝ አቶ አስራት የተባለን ግለሰብ ውሀ ቀድቶ ሲመለስ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች በአደባባይ በጥይት ደብድበው ሲገድሉት አይቻለሁ ብላለች።
ሟች ከመኖሪያ ቤቱ ወጣ ብሎ ከሚገኝ ወንዝ ውሀ በጀሪካን ቀድቶ ሲመለስ መንገድ ላይ አስቆሙት፣ የተሸከመውን ጀሪካን አስወርደው አንበረከኩት፣ መታወቂያውን እያሳየ አትግደሉኝ የልጆች አባት ነኝ እያለ ቢማጸናቸውም ጆሮ ሳይሰጡት ህይወቱን እንደቀጠፉት ማየቷን ገልጻለች።
ይህ ብቻ አይደለም ውሃ ለመቅዳት ወንዝ ሄደው ሲመለሱ ያገኟቸውን ሰዎች በሰልፍ አንበርክከው ግፍ በተሞላበት አኳኋን ጥይት አርከፍክፈው መግደላቸውን መመልከቷን ተናግራለች።
የሟች አቶ አስራት ባለቤትም የትዳር አጋራቸውና የልጆቻቸው አባት በአደባባይ መረሸን ጥልቅ ሃዘን እንደጣለባቸው ገልጸው፤ ቀጣይ የቤተሰባቸው ህይወት አስከፊ አደጋ ላይ መውደቁን ለኢዜአ ተናግረዋል።
የሟች ወንድምም እንደ እናትና አባት ሆኖ ያሳደገኝን ወንድሜን አልቅሰን እንኳን እንዳንቀብር ተከልክለናል ነው ያሉት።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!