Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች 27 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማት ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በጦርነቱ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች 27 ሚሊየን ብር የሚገመት የአልባሳትና የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
 
ኮሚሽኑ አክት አሊያንስ ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት እንዲሁም ከኖርዌይ፣ ዴንማርክ እና ስዊድን ቤተክርስቲያን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው በሸዋሮቢትና አጣየ ከተሞች ለተፈናቀሉ ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ያደረገው።
 
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ይልቃል ሽፈራው የደረሰው ጉዳት የከፋ በመሆኑ ድጋፉ በቂ አይደለም ለአሁኑ የህፃናት አልሚ ምግብን ጨምሮ የዕለት ደራሽ የምግብ ግብዓትና የአልባሳት ድጋፍ አድርገናል ነው ያሉት።
 
ወደፊትም ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ኮሚሽነሩ፥ በተለይም ጉዳት የደረሰባቸውን ማህበራዊ ተቋማት መልሶ በመገንባት ስራ ላይ ትኩረት አድርገን ለመስራት ተዘጋጅተናልም ብለዋል።
 
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ቤተክርስቲያኗ በደረሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ማዘኗን ገልጸዋል።
 
ቤተ ክርስቲያኗ ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመደገፍ ትሰራለች ያሉት ሊቀ ጳጳሱ፥ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውንና የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ በጋራ እንዲተባበር ጠይቀዋል።
 
ድጋፉን የተረከቡት የአጣየ ከተማ ከንቲባ አቶ አሳልፍ ደርቤና የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዘነበ ተክሌ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው፥ በደረሰው ከፍተኛ ውድመት ማህበረሰቡ ለከፋ ችግር በመጋለጡ ሌሎች ግብረሰናይ ድርጅቶችም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
 
በሳምራዊት የስጋት
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.