ኢትዮጵያ በአጎዋ እንድትቆይ በመጠየቅ የኮንግረስ አባል ኬረን ባስ ለዋይት ሃውስ ደብዳቤ አስገቡ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፍተኛ ተሰሚነት ያላቸው የአሜሪካ ኮንግረስ አባል የሆኑት ኬረን ባስ ኢትዮጵያ በአጎዋ እንድትቆይ በመጠየቅ ለፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ደብዳቤ አስገቡ።
የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ለተለያዩ የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ኢትዮጵያ የአጎዋ እድል ተጠቃሚነቷ እንዲቀጥል በመጠየቅ ደብዳቤ ልኳል።
ይህንንም ተከትሎ ነው የኮንግረስ አባሏ ኬረን ባስ ደብዳቤያቸውን ለዋይት ሀውስ ያስገቡት።
ሰሞኑን ከበርካታ የኮንግረስ መሪዎች፣ ከዋይት ሃውስ ባለስልጣናት እንዲሁም ከጥቁር አሜሪካውያን የኮንግረስ እና የሴኔት አባላትና መሪዎች ጋር ውይይት ያደረገው ካውንስሉ፥ ሁሉም ኢትዮጵያ የአጎዋ ተጠቃሚነቷ መቀጠል አለበት ብለው እንደሚያምኑ አንስቷል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!