Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች አገልገሎት መስጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች አገልገሎት መስጠት ጀምረዋል።

በአሸባሪው ህወሓት ቡድን ጉዳት የደረሰባቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደብረ ብርሃን ዲስትሪክት ከ30 በላይ ቅርንጫፎች አስፈላጊውን እድሳትና ቁሳቁስ በማሟላት ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ዲስትሪክቱ በዛሬው እለት ተጨማሪ የኤፌሶንና የካራዳሚ ቅርንጫፎችን አገልግሎት እንዲሰጡ አድርጓል።

ባንኩ ቅርንጫፎቹ በአጭር ጊዜ ጠግኖ እና አስፈላጊውን ቁሳቁስ አሟልቶ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉ እንዳስደሰታቸውም የአካባቢው ነዋሪዎች መግለጻቸውን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.