Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋር እንደመሆኗ መጠን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በአብሮነት ትቆማለች -በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋር እንደመሆኗ መጠን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በአብሮነት ትቆማለች ሲሉ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣዎ ዢዩአ ገለጹ፡፡
አምባሳደር ዣኦ ዢዩአ በፈረንጆች 2022 በአዲስ አመት መልዕክታቸው በቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ዢንፒንግ እና በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ቁርጠኛ አመራር የተገነባው መተማመንን መሰረት ያደረገው የሁለትዮሽ ግኑኝነት የበለጠ እንዲጠናከር እየሰሩ መሆናቸውን አንስተዋል።
የቻይና ኢትዮጵያ አጠቃላይ ስትራቴጂካዊ የትብብር አጋርነት በጥልቀትም ሆነ በስፋት እያደገ በመሄድ ለቻይና-አፍሪካ ግንኙነት አንፀባራቂ ምሳሌ እየሆነ መጥቷልም ነው ያሉት አምባሳደሩ።
ቤጂንግ ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋር እንደመሆኗ መጠን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በአብሮነት እንደምትቆም አምባሳደሩ አረጋግጠዋል።
ሁለቱ ሀገራት አሁን ላይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በጋራ በመታገል ላይ መሆናቸውን አምባሳደር ዣኦ ዚዩአ ማስታወቃቸውን ከኢምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.