የደቡብ ክልል የባህል ስፖርት ውድድርና ፌስቲቫል ዛሬ በይፋ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል 19ኛው የባህል ስፖርት ውድድርና 15ኛው የባህል ስፖርት ፌስቲቫል የመክፈቻ መርሃ ግብር በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
በመርሃ ግብሩ የደቡብ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የስፖርቱ ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል፡፡
አሁን ላይም በክልሉ ከተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች የተውጣጡ ስፖርተኞች በባህላዊ ጭፈራ ፌስቲቫሉን በማድመቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
በ22 አይነት ስፖርታዊ ውድድሮች የሚካሔደው ይህ ስፖርታዊ ውድድርና ፌስቲቫል አንድነት እና ወንድማማችነትን ከማጠናከሩም ባለፈ ወጣቶች የተለያዩ ተሰጥኦቸዉን የሚያጎሉበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።