Fana: At a Speed of Life!

ዩኒቨርሲቲው በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረውን የስነ ልቦና ችግር ለመፍታት ለማህበረሰቡ ስልጠና ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወሎ ዩኒቨርሲቲ በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረውን የስነ ልቦና ችግር ለመፍታት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና ለአካባቢው ነዋሪዎች ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን ገለፀ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ÷ በአሁኑ ወቅት የማህበረሰብ ስነ ልቦና ግንባታ ስልጠና አስፈላጊ ነው ያሉ ሲሆን÷ በጦርነቱ ምክንያት ከወደመው ቁሣቁስ በላይ የተፈጠሩ የስነ ልቦና ጉዳቶች ለመጭው የልማት እንቅስቃሴ እንቅፋቶች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህም በስነ ልቦና ግንባታ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት አለበት ነው ያሉት፡፡

ዩኒቨርሲቲውም የመማር ማስተማር ስራን ከመጀመሩ በፊት በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረውን የስነ ልቦና ችግር ለመፍታት ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እስከ አካባቢው ነዋሪዎች የሚደርስ የማህበረሰብ ሥነ ልቦና ግንባታ ስልጠና እንደሚሠጥ ገልጸዋል፡፡

ስልጠናውን ለመሥጠት በዩኒቨርስቲው የሚገኙ የስነ አዕምሮና የማህበረሰብ ስነ ልቦና ሣይንስ ባለሙያዎች እየተዘጋጁ ይገኛሉ ፤ከዩኒቨርሲቲው መምህራን ውጪም በተጋባዥ ባለሙያዎች ስልጠናው ይታገዛል ብለዋል፡፡

በአለባቸው አባተ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.