Fana: At a Speed of Life!

የተፋሰስ ልማት ለግብርና እድገት መሠረት ነው – ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

የአዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተፋሰስ ልማት ለግብርና እድገት መሠረት መሆኑን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የ2014 የተፋሰስ ልማት ሥራን በክልል ደረጃ በዳሌ ወረዳ ቃሊቴ ሲሚጣ ቀበሌ አስጀምረዋል፡፡

በሲዳማ ክልል በዘንድሮ የተፋሰስ ልማት 546 ነባርና 100 አዳዲስ ተፋሰሶች በአጠቃላይ 646 ተፋሰሶች የሚለሙ ሲሆን፥ ይህም ልማት በ108 ሺህ 296 ሄክታር መሬት ላይ የሚከናወን እንደሆነ አቶ ደስታ ሌዳሞ ገልጸዋል።

የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ መስፍን ቃሬ ፥ የዘንድሮ የተፋሰስ ልማት ከአፈር ልማትና ጥበቃ ባለፈ የበጋ ልማት፣ የአረንጓዴ ልማትና ከንክኪ ነጻ የሆነ አካባቢን መፍጠር ዓላማ ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የግብርና ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ወንዳለ ሐብታሙ በበኩላቸው፥ የተፋሰስ ልማት ከሌለ በግብርናው ዘርፍ የታቀደውን ለማሳካት አዳጋች ይሆናል ነው ያሉት፡፡

የተፋሰስ ልማትን ማጠናከር ለነገ የሚባል ጉዳይ ባለመሆኑ ኅብረተሰቡን በማስተባበር ጠንክረን እንሰራለን ነው ያሉት፡፡

በሲዳማ ክልል በዛሬው ዕለት የተጀመረው የተፋሰስ ልማትም በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የሚተገበር ይሆናል።

በጥላሁን ይልማ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.