የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ የአመራር ግንባታ መድረክ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የአመራር ግንባታ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
“መመረጥ – ተለውጦ ሀገርን ለመለወጥ ” በሚል ርዕስ ለዚህ አላማ የተዘጋጀ ሰነድ ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመድረኩ አላማና ፋይዳ ዙሪያ ለተሳታፊ አመራሮች ገለጻ የሰጡ ሲሆን ፥ አሁን በተጀመረው የአመራር ግንባታ አካሄድ ፓርቲው ብቁ አመራር እየገነባ የጠራ እሳቤ ይዞ እንደሚወጣ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ፥ የውይይት መድረኩ ዋና አላማ አመራር መገንባት ነው ማለታቸውን ከከተማው ብልጽግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ብልፅግና በምርጫ ያገኘው ድልን ሳይሆን ህዝብ የማገልገል ዕድልን መሆኑን የገለፁት ሃላፊው ፥ ይህን ሃላፊነት ለመወጣት የአገልጋይነት መንፈስ ተላብሶ አገራዊ ሃላፊነት በአግባቡ የሚወጣ አመራር ማብቃት ያስፈልጋል ብለዋል።
የአመራር የተግባር ጥንካሬና የፓርቲ ስነ ምግባር ከፍ በማድረግ የእያንዳንዱ አመራር ጥንካሬ እየጎለበተ ድክመት የሚታረምበት መድረክ እንደሆነም አስረድተዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!