Fana: At a Speed of Life!

ከአማራና አፋር ክልሎች የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸዉ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአማራና አፋር ክልሎች በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ወረራ ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው የማስመለሱ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የፌዴራል አደጋና ሥጋት አመራር ኮሚሽን ገለጸ።

ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ÷ በጦርነቱ ከሁለቱ ክልሎች 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ዜጎች እንደተፈናቀሉም ነው የተናገሩት።

ከቀያቸው ከተፈናቀሉት 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ያህል የአማራ ክልል ነዋሪዎች ዉስጥ 1 ነጥብ 2 ሚሊየን የሚሆኑት ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው ተመልሰዋልም ብለዋል ኮሚሽነሩ።

ሰሞኑን አሸባሪው ቡድኑ በአፋር ክልል ዞን አንድ ውስጥ በሚጠቃለሉት አምሥት ወረዳዎች በከፈተዉ ጦርነት ተጨማሪ 200 ሺህ ዜጎች መፈናቀላቸዉን እና ቀድሞ ከተፈናቀሉት ጋር በድምሩ 600 ሺህ እንደደረሱ ነው የጠቆሙት።

ህወሓት ዳግም ክልሉን ከመውረሩ በፊት የተፈናቀሉትን ወደ ቀያቸው ለመመለስም እየተሰራ መሆኑን ነው ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ የተናገሩት።

ወደ ቀያቸዉ የተመለሱትን ዜጎች በቋሚነት ለማቋቋምም እየተሠራ ነው ብለዋል።

በጀማል ከዲሮ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.