ሀገርን ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሻገር ብቃት ያለው አመራር የመፍጠር ስራን አጠናክረን እንቀጥላለን- አቶ ርስቱ ይርዳ
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገርን ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሻገር ብቃት ያለው አመራር የመፍጠር ስራን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ገለጹ፡፡
የደቡብ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች “መመረጥ ተለውጦ ሀገርን ለመለወጥ” በሚል መሪ ሀሳብ የአመራር ግንባታ የውይይት መድረክ በሀዋሳ እያካሄዱ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በውይይት መድረኩ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳን ጨምሮ፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችም እየተሳተፉ ይገኛሉ።
“የመድረኩ አላማ በየደረጃው ያለው አመራር ለውጡን ከመምራት አኳያ እንዲሁም ህዝቡ በምርጫ የሰጠውን እድል ተጠቅመን ለህዝባችን የገባነውን ቃል የምንፈጽምበት ነው” ሲሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ ተናግረዋል፡፡
ሀገርን ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሻገር ብቃት ያለው እና ጠንካራ አመራር የመፍጠር ስራን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም ጠቁመዋል።
በጦርነት ፣ በግጭት፣ በመጠፋፋት፣አንዱ አንዱን በማሳደድ ኢትዮጵያ ትውልዶቿን እያጣች በመሆኑ ይህንን ታሪክ መቀየር ይገባል ሲሉም አብራርተዋል።
ለውጡን ለመቀልበስ የሚፈልጉ ሀይሎች ብልጽግና የተነሳበትን አላማ ከግብ እንዳያደርስ ለማሰናከል ሰፊ ጥረት መደረጉንም ጠቁመዋል።
“በፓርቲያችን ውስጥ ያሉ ችግሮችን መመርመር እና መፈተሽ፣ በየደረጃው የአመራር ጥራት እንዲጠበቅ ማድረግ እና የህዝብ አገልጋይነትን ማረጋገጥ ይገባናል” ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!