የደቡብ ምዕራብ የኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል “መመረጥ ተለውጦ ሀገርን ለመለወጥ” በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ የኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል “መመረጥ ተለውጦ ሀገርን ለመለወጥ” በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጸጋዬ ማሞ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን፥ ለመድረኩ በተዘጋጀው ሰነድ ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡
ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ፥ “ትክክለኛ የብልጽግና አስተሳሰቦችና የብልጽግና መሠረታዊያንን ለይተን የአመራሩንና የአባላት አቅም ለመገንባት ሁሉም የፖለቲካ አመራር ራሱ በቅቶ ሌሎችን ማብቃት ይገባዋል” ብለዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ጸጋዬ ማሞ የመድረኩ ዋና ዓላማ አመራሩን ለይቶ ለፓርቲው ህልውና ብቁ አመራር መፍጠር፣ መገንባትና ማብቃት ስህተቶች ካሉም ማረም ነው ማለታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!