Fana: At a Speed of Life!

አቶ አህመድ ሺዴ ከሳዑዲ አረቢያ የገንዘብ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ከሳዑዲ አረቢያ የገንዘብ ሚንስትር መሀመድ ቢን አብደላህ አል ጀዳን ጋር ተወያይተዋል::

በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የተመራ እና ከመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች የተውጣጣ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት የበለጠ ስለሚጠናከርበት እንዲሁም በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙ ዜጎች የአጭር ጊዜና ዘላቂ መፍትሄዎች ስለሚያገኙበት ሁኔታ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ለመምከር አልሞ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ማቅናቱ ይታወሳል፡፡

ቡድኑ ባለፉት ቀናት በነበረው ቆይታ በሪያድ ከኢትዮጵያ ኮሙኒቲ አመራሮች እና አባላት፣ ከሀይማኖት መሪዎች እንዲሁም የንግዱ ማህበረሰብ ጋር ተወያይቷል፡፡

ልዑኩም በትናንናው እለት በሳዑዲ አረቢያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረገ ሲሆን ÷በዛሬው ዕለት ደግሞ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ከሳዑዲ አረቢያ አቻቸው መሀመድ ቢን አብደላህ አል ጀዳን ጋር መወያየታቸውን ከሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.