Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ የጤና አገልግሎትና ተደራሽነትን ለማጎልበት በትኩረት እየተሰራ ነው- አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል የጤና አገልግሎትና ተደራሽነትን ለማጎልበት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ፡፡
 
በሀረሪ ክልል ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው ጤና ጣቢያ ዛሬ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
 
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መሰተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ባደረጉት ንግግር ÷ የክልሉ መንግስት ለህዝብ የገባውን ቃል የማህበራዊንና የኢኮኖሚ ጥያቄዎችን ለመመለስ ርብርብ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
 
በተለይም የጤና አገልግሎት ጥራትን ለማጎልበትና ተደራሽነትን ይበልጥ ለማረጋገጥ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ነው የተናገሩት።
 
የተመረቀው ጤና ጣቢያ የአካባቢው ማህበረሰብ ለረጅም ጊዜ ሲጠይቀው የቆየ ጥያቄ መሆኑን አንስተው÷ የፕሮጀክቱን የግንባታ ወጪ ለሸፈነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምስጋና አቅርበዋል።
 
ጤና ጣቢያው ህብረተሰቡ በሚፈልገው ደረጃ አገልግሎት እንዲሰጥ በማስቻል በተለይም የእናቶችና የጨቅላ ህፃናትን ሞት ከመቀነስ አንፃር ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።
 
የክልሉ መንግስት ተቋሙን በሰው ሃይል፣ በአደረጃጀትና በግብዓት የተሟላ እንዲሆንና ለሌሎች ጤና ተቋማትም ሞዴል እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ነው ያሉት።
 
የጤና ባለሙያዎችም ሙያዊ ስነምግርና ብቃትን ባሟላ መልኩ ህብረተሰቡን እንዲያገለግሉ አሳስበው የጤና ባለሙያዎቹን ጥያቄ ከመመለስ አንፃርም ርብርብ ይደረጋል ሲሉ ተናግረዋል።
 
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኢብሳ ሙሳ በበኩላቸው÷ ጤና ጣቢያው ተገንብቶ አገልግሎት ለማስጀመር ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ተቁመዋል፡፡
 
በአሁኑ በጤና ጣቢያው ወቅት አስፈላጊ የሆኑ የህክምና ቁሳቀሶችና መድሃኒቶች መሟላታቸውን የገለጹት ሃላፊው÷ተቋሙ የቀዶ ጥገና አገልግሎትን ጨምሮ ሌሎች የህክምና አገልግሎቶች እንደሚሰጥ መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.