Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ35ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር ቆይታ ማድረጋቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ እንደተናገሩት÷ ከጉባኤው ጎን ለጎን በተካሄደው የመሪዎቹ የሁለትዮሽ ምክክር ላይ የሀገራቱን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ÷ ከዚምባቡዌ መሪው ኤመርሰን ምንጋግዋ ጋር ውይይት ያካሄዱ ሲሆን ÷የአፍሪካን ደምጽ በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲሰማ ለማስቻል በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ÷ኢትዮጵያ የተፈጠረባት የውጭ ጫና ተቋቁማ ችግሯን በራሷ መንገድ ለመፍታት የሄደችበትን ጥረትም አድንቀዋል።

ሁላችንም ኢትዮጵያን ስናስብ የአፍሪካዊ ታሪካችን መሠረት እንደሆነች እናስባለን ያሉ ሲሆን÷ ሀገሪቱ በግብርናው መስክ እየሰራች ያለውን ስራም አድንቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው ÷የአፍሪካን ዘላቂ ችግር ለመፍታት ግብርና ላይ መሰረት ያደረገ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ አሳውቀዋል።

በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ሙሀመዱ ቡሀሪ ጋር የተወያዩ ሲሆን÷ መሪዎቹ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በበለጠ ወደፊት ሊያራምዱ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በተለይም አፍሪካ ድምጽ ሊሆን የሚችል ሚዲያን ለማቋቋም ሀገራቱ በጋራ ሊረባረቡ እንደሚገባ ነው የጠቆሙት።

ፕሬዚዳንት ቡሃሪ ኢትዮጵያ በግብርና ላይ እየሰራች ያለውን ስራ ያደነቁ ሲሆን÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፕሬዚዳንቱ ሙስናን ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረትም አድንቀዋል።

በብስራት መለሰ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.