ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክስርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይታቸውን አስመልክተው ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ ዛሬ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያሪክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘ አክሱም ወጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጋር የተሳካ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ከቅድስት ቤተክርስቲያን በኩል የሚነሱትን ጉዳዮችን ህጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ በውይይት መፍታት እንደሚቻል ተግባብተናል ሲሉም አስፍረዋል ።
ስለ መልካምና ገንቢ ቆይታም ለቅዱስነታቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!