Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ የሚያስፈልጋትን ጠንካራ አፍሪካዊ ሚዲያ እውን ለማድረግ በጋራ መስራት ይገባል – ጋዜጠኞች

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ የሚያስፈልጋትን አንድ ጠንካራ አፍሪካዊ ሚዲያ እውን ለማድረግ በጋራ መስራት ይገባል ሲሉ በ35ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የታደሙ ጋዜጠኞች ተናገሩ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ለአፍሪካ 24 (Africa24) በግሉ የሚጽፈው አህመድ ኢብራሂም እና የሲ ጅ ቲ ኤን ዘጋቢው ግሩም ጫላ፥ የአፍሪካን እውነታ እና ብዝሃ ማንነት ለተቀረው ዓለም ለማስረዳት ጠንካራ ሚዲያ መገንባት ይገባል ብለዋል።

የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤን እውን በማድረግ አፍሪካውያንን ወደ ትብብር ለማምጣት የሚጠበቀው ጠንካራ ሚዲያ ወሳኝ ሚና እንዳለውምጋዜጠኞቹ አብራርተዋል።

በኦቢኤን ሆርን ኦፍ አፋሪካ ላይ የአረብኛ ክፍል አርታኢ የሆነው መሀመድ ሻፊ እንዲሁም በፕራይም ሚዲያ የእንግሊዝኛ ክፍል ዘጋቢዋ ልደት ሙለታ ÷ የአፍሪካን እሴቶች ከፍ ባለ ደረጃ ለማስተዋወቅ እና በመስኩ ያለውን የውጭ ተጽዕኖ ለመግታት ጠንካራ አፍሪካዊ ሚዲያን በቶሎ ወደ ስራ ማስገባት ያስፈልጋል ብለዋል።

በእውቀት ለይ ተመስርቶ አፍሪካዊ የጋራ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት አንድ አውድ የሆነ ሚዲያን ስራ ላይ ለማዋል መንግስታት የአፍሪካ ኅብረት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻዎች ሊተባባሩ እንደሚገባም ጋዜጠኞቹ አሳስበዋል።

በአወል አበራ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.