Fana: At a Speed of Life!

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ የካቲት1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር የሚጀምር መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አበበ ግርማ ገለጹ።

በአሸባሪው ህወሃት ውድመትና ዘረፋ የተፈፀመበት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የመልሶ ጥገና ስራ በማከናወን ከየካቲት 7 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የማታ ተማሪዎችን በመቀበል ስራውን የሚጀምር ሲሆን÷ በተከታይም የመጀመሪያ አመትና ተመራቂ ተማሪዎችን ይቀበላል ተብሏል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አበበ ግርማ ÷ዩኒቨርሲቲው በአሸባሪው ህወሓት ከ6 ቢሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ሃብት ዘረፋና ውድመት የደረሰበት መሆኑን አስታውሰው የተለያዩ ጥረቶች ተደርገው ለዳግም የመማር ማስተማር ሂደት ዝግጁ ሆኗል ብለዋል።

ከሌሎች ዘጠኝ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ባገኘው ድጋፍ በመጀመሪያው ምእራፍ ዳግም ስራ ለመጀመር የሚያስችለው ደረጃ ላይ ይገኛልም ነው ያሉት።

በቀጣይም ከመንግስት፣ ከበጎ አድራጊዎችና ከቀድሞ ተማሪዎች ጋር በመሆን ዩኒቨርሲቲውን የማሟላት እቅድ መያዙን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ በመሆኑ ወላጆች ልጆቻቸውን ያለምንም ስጋት ወደ ዩኒቨርሲቲው እንዲልኩ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ዶክተር አበበ ።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.