በመዲናዋ በበጀት ዓመቱ 3ኛ ሩብ ዓመት ከ3 ሺህ በላይ አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በበጀት ዓመቱ 3ኛ ሩብ ዓመት ከ3 ሺህ በላይ አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን የከተማዋ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ ሶስተኛ ሩብ ዓመት 2 ሺህ 698 አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለመስጠት አቅዶ 3 ሺህ 5 ፈቃዶችን መስጠቱ ተመላክቷል፡፡
አፈጻጸሙ 111 በመቶ መሆኑን የገለጸው ኮሚሽኑ ÷ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸርም የ 8 ነጥብ 6 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ጠቁሟል፡፡
አፈጻጸሙ አዲስ አበባ ላይ ያለው የኢንቨስትመንት ፍሰት አበረታች መሆኑን አመላካች ነው መባሉን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!