ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሰላምና ለሀገር ደኅንነት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከግጭትና ከሽብር ራሱን አርቆ፣ ለሰላምና ለሀገር ደኅንነት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ።
የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ከመከረ በኋላ መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫውም ከለሰላምና ከሀገር ደኅንነት በተቃራኒው ተሰልፎ የሚገኝ ማንኛውም ሰው፣ አካልና ቡድን ላይ ሕጉ የሚፈቅደውን ተገቢውን ሕግና ጸጥታ የማስከበር ሥራ የምንሠራ መሆኑን እናሳውቃለን ብሏል።
መጭው ቀናት ለሕዝበ ክርስቲያኑም ሆነ ለሕዝበ ሙስሊሙ የበዓላት ሰሞን እንደመሆኑ መጠን አማኞች በትብብርና በመግባባት የጠላቶቻችንን ፍላጎት በማክሸፍና የጋራ ደህንነታችንን በማረጋገጥ እንደ ሀገር የተሳካ ጊዜያት እድንናሳልፍ የደህንነት ምክር ቤቱ አበክሮ ይጠይቃል ብሏል።
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦