ሀገራችን በምታልፍበት የሁኔታዎች መውጣትና መውረድ፣ በሙላትና በጉድለት ሁሉ ማመስገን ይገባል -የመካነኢየሱስ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ምዕመናን
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራችን በምታልፍበት የሁኔታዎች መውጣትና መውረድ፣ በሙላትና በጉድለት ሁሉ ማመስገን ይገባል ሲሉ የመካነኢየሱስ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ምዕመናን ተናገሩ።
ዛሬ ሀገራዊው የምስጋና መርሐ ግብር በአምስት ኪሎ መካነኢየሱስ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ተካሂዷል።
በሃይማኖት፣ በማንነትና በሌሎች ማህበራዊ ፓለቲካ ፈተናዎች አልፈን እዚህ መድረሳችን ትልቅ ዋጋ ስላለው ማመስገን ይገባል ነው ያሉት አማኞቹ።
ሀገሪቱ በጦርነትና በአየር ሁኔታ ለውጥ ምክንያት የደረሱባትን ፈተናዎች ተጋፍጣ ማለፍ መቻሏን በማሰብ ማመስገን ተገቢ መሆኑን ያነጋገርናቸው የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን ተናግረዋል።
የዕለቱ የምስጋና መርሐ ግብር በዝማሬ፣ በጸሎትና በእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት ተከናውኗል።
በበርናባስ ተስፋዬ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!