አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20 ፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዡ ቢንግ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የኢትዮጵያ እና ቻይናን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ከአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ጋር በተያያዘ ሀገራቱ ሊኖራቸው በሚችለው የሁለትዮሽ ትብብር እና ኢኒሼቲቩን ማሳደግ በሚችሉበት አግባብ ዙሪያ መወያየታቸውን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
ከዚህ ባለፈም ለአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የድርጊት መርሐ ግብር ተግባራዊነት በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን ሁለቱ ወገኖች አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡